አርባ ምንጭ ውኃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በአዲስ መልክ እየተከለሰ በሚገኘው የዩኒቨርሲቲው የሴኔት መተዳደሪያ ደንብ (Senate legislation) ረቂቅ ላይ ከኢንስቲትዩቱ መምህራን ጋር ታኅሣሥ 16/2017 ዓ/ም ውይይት አካሂዷል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የኢንስቲትዩቱ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ተወካይ ዶ/ር ታምሩ ተሰሜ እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው ራዝ ገዝ እንዲሆን ከዝግጅት ምዕራፍ ሥራዎች አንዱ የሆነው የሴኔት መተዳደሪያ ደንብን መከለስ በመሆኑ የተዘጋጀው ረቂቅ ከመጽደቁ በፊት አስተያየቶች እንዲሰበሰቡ እንደ ዩኒቨርሲቲ አቅጣጫ በመቀመጡ ውይይቱ ተዘጋጅቷል፡፡ በውይይቱ የተነሱ ሃሳቦችና አስተያየቶች ተደራጅተው ለሚመለከተው አካል የሚቀርቡ መሆኑንም ዶ/ር ታምሩ አስረድተዋል፡፡

የኢንስቲትዩቱ መምህር ሙሳ ሙሃባ ዩኒቨርሲቲው ትምህርት ሚኒስቴር ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ራስ ገዝ ለመሆን ጉዞ በመጀመሩ የቀድሞውን መተዳደሪያ ደንብና በቅርቡ ራስ ገዝ የሆነው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ተሞክሮ በማየት በተዘጋጀው መተዳደሪያ ደንብ ላይ ከተሳታፊዎች ጠቃሚ አስተያየቶች የተሰጡ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ መሰል ውይይቶች በረቂቅ ሰነዱ ላይ መካሄዳቸው መተዳደሪያ ደንቡን የተሻለና ውጤታማ እንዲሆን ያስችላሉ ብለዋል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት