የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ STEM ሥልጠና ማዕከል በአርባ ምንጭና አካባቢዉ ከሚገኙ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጡ 131 የ9ኛና 10ኛ ክፍል ተማሪዎች በሮቦቲክስ ቴክኖሎጂና በሌሎች ሣይንስ ትምህርት ዘርፎች ላይ ትኩረቱን ያደረገ የተግባር ሥልጠና ከጥር 26- 30/2018 ዓ.ም ድረስ ሰጥቷል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የዩኒቨርሲቲው STEM ማዕከል አስተባባሪ ዶ/ር ቢኒያም ወንዳለ ሥልጠናው በዋናነት በተፈጥሮ ሳይንስ መስክና በአይ ሲ ቲና በሮቦቲክስ ቴክኖሎጂ ላይ ትኩረቱን አድርጎ የተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስና ሒሳብ ትምህርት ሥልጠናዎች በአባያ ካምፓስ በሚገኙ ቤተ-ሙከራዎች የተሰጡ ሲሆን የአይ ሲ ቲና ሮቦቲክስ ሥልጠናዎች በዋናው ግቢ በሚገኙ ቤተ-ሙከራዎች የተሰጡ መሆኑን ዶ/ር ቢኒያም ጠቁመዋል፡፡ ተማሪዎች በትምህርት ቤታቸዉ በንድፈ ሃሳብ ደረጃ የተማሩትን በዩኒቨርሲቲው ውስጥ በሚገኙ ቤተ-ሙከራዎች በተግባር ተለማምደው የፈጠራ ክሂሎታቸውን እንዲያዳብሩና ከቴክኖሎጂ ጋር እንዲተዋወቁ ማስቻል የሥልጠናው ዓለማ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲው የኤሌክትሪካልና ኮምፒውተር ምኅንድና ፋከልቲ መምህርና አሠልጣኝ  ኃ/ማርያም ሙጨ በሥልጠናው ተማሪዎች የሮቦቲክስ ቴክኖሎጂ የደረሰበትን አሁናዊ ደረጃ የማሳወቅና ሮቦት ለመስራት የሚረዱ ጉዳዮችን በተግባር አይተዋል ብለዋል፡፡

የዩኒቨርሲተዉ የኮምፒውቲንግና ሶፍትዌር ምኅንድስና ፋከልቲ  መ/ርና አሰልጣኝ አባይ ኃ/ማርያም በሥልጠናው በዋናነት ተማሪዎቹ መሠረታዊ የኮምፒውተር ዕውቀትና ክሂሎት እንዲኖራቸውና ቴክኖሎጂው የደረሰበትና ደረጃ በተግባር እንዲያዩትና እንዲለማመዱት ተደርጓል ብለዋል፡፡ ከጫሞ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመጣችው ተማሪ ትዝታ ሳሙኤል በሰጠችዉ አስተያየት በሥልጠናው ብዙ ነገር እንደተማረች ገልጻ በተለይ ነገሮችን ከጽነሰ ሃሳብ በለፈ በተግባር እንድታይ የረዳት መሆኑን ተናግራለች፡፡


አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት