የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ኅብረት የ2017 ዓ/ም የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምን የካውንስሉ አባላትና የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት መጋቢት 14/2017 ዓ.ም ግምግሟል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
የኅብረቱን የስድስት ወራት ሥራ አፈጻጸም ከመገምገም ባሻገር ከትምህርት ሚኒስቴር የወረደውን የተማሪዎች ኅብረት አደረጃጀት መመሪያን ማስተዋወቅ፣ ከመማር ማስተማር፣ ከትምህርት ጥራትና ከሌሎች የአስተዳደራዊ ጉዳዮች ጋር ተያይዞ የተከናወኑ ተግባራትና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ በዕለቱ ውይይት ተካሂዷል፡፡
የተማሪዎች ኅብረት ፕሬዝደንት ተማሪ ሶፎኒያስ ፈንቴ እንደገለጸው የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ኅብረት በመጀመሪያው መንፈቀ ዓመት ያከናወናቸውን ተግባራትና አፈጻጻም ለመፈተሽ እንዲሁም ደካማና ጠንካራ ጎኖችን ለይቶ ወደ ቀጣይ የሥራ ምዕራፍ ለመግባት የውይይት መድረኩ ተዘጋጅቷል፡፡ ውይይቱ በዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት በቀጣይ የተሻለ የመማር ማስተማር ሥርዓት እንዲኖር ለማድረግ መደረግ በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ የጋራ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ መሆኑንም ተናግሯል፡፡
ከመማር ማስተማር፣ ከትምህርት ጥራት፣ ከተማሪዎች የምግብና የመኝታ አገልግሎት ጋር የተያያዙና ሌሎች ጥያቄዎች ከታዳሚዎች ተነስተው ከመድረክ ምላሽ የተሰጠባቸው ሲሆን ኅብረቱ አዲስ ለተመደቡ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች የመልካም ሥራ ዘመን ምኞት መግለጫ ስጦታ አበርክቶላቸዋል፡፡
በዕለቱ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ኢ/ር አብደላ ከማልን ጨምሮ ም/ፕሬዝደንቶች፣ የፕሬዝደንት ጽ/ቤት ኃላፊ፣ ዳይሬክተሮች፣ የኮሌጅ ዲኖችና የተማሪዎች ኅብረት ሥራ አስፈጻሚዎች እንዲሁም ተማሪዎች ታድመዋል፡፡
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት