በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በማኅበራዊ ሳይንስና ሥነ ሰብ ኮሌጅ በ"Geography and Environmental Studies" ትምህርት ክፍል በ"Environment and Natural Resource Management" ትምህርት ፕሮግራም የ3ኛ ዲግሪ ትምህርቱን ሲከታተል የቆየው የዕጩ ዶ/ር ወርቅአፈራሁ አመነሸዋ የመመረቂያ ጽሑፍ ዛሬ ታኅሣሥ 05/2017 ዓ/ም የውጭና የውስጥ ገምጋሚዎች እንዲሁም አማካሪዎች በተገኙበት ቀርቦ ተገምግሟል፡፡ የመመረቂያ ጽሑፉም አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላቱ በአማካሪ ቦርዱ ተቀባይነት አግኝቶ ጸድቋል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

ዕጩ ዶ/ር ወርቅአፈራሁ አመነሸዋ የመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያጠናቀቀ ሲሆን የመጀመሪያ ዲግሪውን በ"Social Anthropology" እንዲሁም የ2ኛ ዲግሪውን  በ"Geography and Environmental Study" ትምህርት ዘርፍ በ "GIS, Remote Sensing Digital Cartography" ስፔሻላይዝድ አድርጎ ተመርቋል፡፡ 

ዕጩ ዶ/ር ወርቅአፈራሁ የ3ኛ ዲግሪውን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሲከታተል ቆይቶ የመመረቂያ ጽሑፉን "LAND USE LAND COVER DYNAMICS, FOREST BIODIVERSITY MANAGEMENT AND LIVELIHOOD STRATEGIES: IN SHEKA BIOSPHERE RESERVE, SOUTHWEST ETHIOPIA " በሚል ርእስ አከናውኗል፡፡ የዕጩ ዶክተር ወርቅአፈራሁ ውጤት ለዩኒቨርሲቲው ሴኔት ቀርቦ ተቀባይነት ሲያገኝ የሚመረቅ ይሆናል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት