የተከበራችሁ የመላው የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ፣ ውድ ተማሪዎቻችን፣ መምህራን፣ የአስተዳደር ሰራተኞች እና የዩኒቨርሲቲያችን ወዳጆች በሙሉ፤

 

በቅድሚያ አሮጌውን 2018 . ሸኝተን ለዲሱን 2019 . የዘመን መለወጫ በሰላም፣ በፍቅር እና በጤና ስለደረስን እንኳን አደረሳችሁ! እያልኩኝ አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የጤና፣ የስኬት እና የደስታ ዘመን እንዲሆንላችሁ በራሴ እና በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ስም ከልብ የመነጨ የመልካም ምኞት መግለጫዬን አስተላልፋለሁ።

ለፈው 2018 . በዩኒቨርሲቲያችን በርካታ ታሪካዊ ስኬቶች የተመዘገቡበት እና ለቀጣይ እድገታችን ጠንካራ መሰረት የተጣለበት ዓመት ነበር። ዩኒቨርሲቲያችን 2019 . ወደ ራስ ገዝነት (Autonomy) ከሚሸጋገሩ የሀገራችን ቀዳሚ ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ እንዲሆን አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማጠናቀቅ በትምህርት ሚኒስቴር ገለልተኛ ገምጋሚዎች ቡድን  የዝግጁነት ግምገማ ተካሂዶ የትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔን በመጠባበቅ ላይ እንገኛለን፡፡

 

በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲያችን ከኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር በዓለም አቀፍ የሜትሮሎጂ ድርጅት (WMO) የምሥራቅ አፍሪካ የሜትሮሎጂ እና የአየር ንብረት ሥልጠና ማዕከል ሆኖ መመረጡ ተቋማችን በምርምር፣ በፈጠራ እና በሳይንስ ዘርፍ ያለውን የልኅቀት ማዕከልነት በዓለም አቀፍ ደረጃ ያረጋገጠበት ሌላው አበይት አጋጣሚ ነው።

 

ትምህርትና ምርምር ዘርፍ ከተመዘገቡት አበይት ስኬቶች መካከል የዩኒቨርሲቲያችን ሁለት የምርምር ጆርናሎች ማለትም OMO International Journal of Sciences እና Ethiopian Journal of Engineering and Technology በትምህርት ሚኒስቴር ሀገር አቀፍ እውቅና ማግኘታቸው ይጠቀሳል። በዚህም ስኬት ዩኒቨርሲቲያችን ከሚያሳትማቸው አምስት ጆርናሎች መካከል አራቱ ሀገር አቀፍ እውቅና ማግኘት የቻሉ ሲሆን፣ ይህም የዩኒቨርሲቲያችንን የምርምር ጥራትና የሳይንሳዊ ህትመቶች ተደራሽነት ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ ነው።

 

ጤናው ዘርፍ የማስተማሪያና ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታላችን ተኝቶ ህክምናን ጨምሮ አጠቃላይ የህክምና አገልግሎት ማስፋፊያን በማስመረቅ፣ ዘመኑ የደረሰባቸውን የህክምና ቴክኖሎጂዎች በግንባር ቀደምትነት በመታጠቅ የአርባ ምንጭና የአካባቢዋን፣ የደቡብ ኢትዮጵያን ህዝቦች ተጠቃሚ የሚያደርግ እና የህክምና ቱሪዝምን የሚያሳድግ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል። በሌላ በኩል ከጋሞ ዞንና ከአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር በአባያ ካምፓስ የሚገኘውን የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ ደረጃ በማሻሻል ለኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች፣ ለክልላዊና ሀገር አቀፍ ኩነቶች ዝግጁ የማድረግ ስራ ተከናውኖ የዩኒቨርሲቲያችን አባያ ካምፓስ ስቴዲየም የ2019 ዓ/ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ከሚደረግባቸው ስቴዲየሞች መካከል አንዱ ሆኖ ተመርጧል። ይህም የውስጥ አቅምን ማሳደግ ለመማር-ማስተማርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፈ-ብዙ ጥቅም ከመስጠቱም በላይ ተቋሙ ወደ ራስ-ገዝነት ለሚያደርገው ሽግግር ተጨማሪ የገቢ ምንጭ የሚፈጥር ነው፡፡

 

በማኅበረሰብ ጉድኝት ዘርፍም ዩኒቨርሲቲያችን በርካታ ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል።

 

ውድ የዩኒቨርሲቲያችን ማህበረሰብ፤

 

እነዚህ የተመዘገቡት አበይት ስኬቶች የመጡት በሁላችንም የተቀናጀ ጥረት እና በሰራተኞቻችን የላቀ ቁርጠኝነት ነው። በመሆኑም ለዚህ ውጤት በሙሉ አቅማቸው ለሰሩት  የዩኒቨርሲቲያችን  ሰራተኞች እና ለመላው ማህበረሰብ ምስጋናዬ የላቀ ሲሆን፣ ዩኒቨርሲቲያችንም በሀገር አቀፍ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በላቀ ደረጃ ታዋቂ እና ተወዳዳሪ እንዲሆን የተጀመረው ጥረት በአዲሱ ዓመትም ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።

 

አዲሱ 2019 . የጀመርናቸውን ታላላቅ ራዕዮች የምናሳካበት፣ የመማር ማስተማር እና የምርምር ጥራታችንን የበለጠ የምናሳድግበት፣ እንዲሁም ዩኒቨርሲቲያችንን በዓለም አቀፍ ደረጃ በግንባር ቀደምትነት የምናቆምበት የስኬት ዓመት እንዲሆንልን መልካም ምኞቴን አስተላልፋለሁ።

 

በድጋሚ እንኳን 2019 አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ!

/ / አብደላ ከማል

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት