ማስታወቂያ
አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ እንኳን ለ2012 የትምህርት ዘመን በሰላምና በጤና አደረሳችሁ እያለ ለነባርና በ2012 ዓ/ም አዲስ ለተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት የማድረጊያ ቦታና የምዝገባ ጊዜያትን ከዚህ በታች በተገለፀው መሰረት እናሳውቃለን፡፡

የምዝገባ ቀናት
•    ነባር 2ኛ ዓመት እና ከዚያ በላይ መደበኛ የቅድመ ምረቃ፣ የድህረ-ምረቃ እና የተከታታይና ርቀት ተማሪዎች ከመስከረም 21-22, 2012 ዓ.ም
•    አዲስ የተመደባችሁ የቅድመ-ምረቃ መደበኛ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ከመስከረም 28-29, 2012 ዓ.ም
•    አዲስ ያመለከታችሁ እና የመግቢያ ፈተና ያለፋችሁ የተከታታይና ርቀት ተማሪዎች ከመስከረም 28-29, 2012 ዓ.ም
•    አዲስ ያመለከታችሁ እና የመግቢያ ፈተና ያለፋችሁ የድህረ-ምረቃ ተማሪዎች ከመስከረም 28-29, 2012 ዓ.ም
ሪፖርት የማድረጊያ ቦታ
የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እና የውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተማሪዎች………………………  በዋናው ካምፓስ
•    የህክምናና ጤና ሣይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች   ………………………በነጭ ሣር ካምፓስ
•     የተፈጥሮ ሣይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች  ……………………………..……በአባያ ካምፓስ
•    የግብርና ሣይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች ………………………………………በኩልፎ ካምፓስ
•    የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ እንዲሁም የማህበራዊ ሣይንስና ስነ-ሰብ  ኮሌጅ ተማሪዎች………በጫሞ  ካምፓስ
•     የፔዳጎጂ እና ብሄቨየራል ሳይንስ እንዲሁም የህግ ት/ቤት ተማሪዎች  …………….………… በጫሞ  ካምፓስ
•     የሳውላ ካምፓስ ተማሪዎች      ……………………………………………………………………………………… በሳውላ ካምፓሰ        
ማሳሰቢያ፡ አዲስ የተመደባችሁ የዩኒቨርስቲው የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው በምትመጡበት ወቅት
•    የመሰናዶ ትምህርት(11ኛ እና 12ኛ ክፍል)  ትራንስክሪፕት ዋናውን ከ 2 ኮፒ ጋር    
•    የ10 እና የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዋናውን ከ 2 ኮፒ ጋር
•    ሦስት በአራት የሆነ 4(አራት) ጉርድ ፎቶግራፍ
•    እንዲሁም ለግል መገልገያ የሚሆን እንደ አንሶላ ፤ትራስ ልብስ ፤ የስፖርት ትጥቅና የመሣሰሉትን ይዘው መምጣት ይጠበቅባችኃል፡፡
•    ተማሪዎች በየካምፓሶቻችሁ  በተጠራችሁበት ቀናት ሪፖርት እንድታደርጉ እያሣሰብን ቀደም ብለው ወይም ዘግይተው ለሚመጡ ተማሪዎች ምንም ዓይነት አገልግሎት እንደማይሰጣቸው ያስታውቃል፡፡
•    ይህንን ማሳሰቢያ ተላልፈው በሚመጡ ተማሪዎች ላይ ለሚደርሰው መጉላላት ዩኒቨርሲቲው ተጠያቂ አይሆንም፡፡

የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አ/ዳ/ጽ/ቤት