ማስታወቂያ ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ2011 የትምህርት ዘመን መደበኛ ፕሮግራም ተመረቂ ተማሪዎች በሙሉ

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ2011 የትምህርት ዘመን በመደበኛ መርሃ-ግብር ወንድ-3.5 እና ከዚያ በላይ፣  ሴት 3.25 እና ከዚያ በላይ ውጤት ለተመረቁ ተማሪዎች በ2012 የትምህርት ዘመን ነፃ የ2ኛ ዲግሪ ትምህርት ዕድል አወዳደሮ በመስጠት ለማስተማር የሚፈልግ መሆኑን እየገለፀ፤ ከመስከረም 09-14/2012 ዓ/ም ድረስ ባሉት የሥራ ቀናት እንድትመዘገቡና የዕድሉ ተጠቃሚ እንድትሆኑ ይጋብዛል፡፡

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ የትምህርት ማስረጃዎች፡-

  • ጊዜያዊ ዲፕሎማ / Temporary Diploma/
  • የተማሪ ውጤት መግለጫ /Student Copy/
  • የድጋፍ ደብዳቤ /Recommendation Letter/
  • በተለያዩ የተማሪ አደረጃጀቶች አገልግሎት የተሰጠበት የምስክር ወረቀት

የምዝገባ ቦታ፡-  ሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ