
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ የማኅበረሰብ ጉድኝት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከጋሞ ዞን ሥራ ዕድል ፈጠራ መምሪያ ጋር በመተባበር ከሙዝ ልጣጭ በሚገኝ ስታርች እና ከዓሣ ቅርፊት በሚገኝ ቺቶሳን ውሕድና የሚበላ ፖሊመር በመጠቀም በአካባቢው የሚገኙ ፍራፍሬዎችን የቆይታ ጊዜ ማራዘም የሚያስችል ምርምር ውጤትን ወደ ማኅበረሰቡ ለማውረድ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: ፍራፍሬዎች ሳይበላሹ ማቆየት የሚያስችል የምርምር ውጤትን ወደ ማኅበረሰቡ ለማውረድ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ

- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሕግ ት/ቤት ከየ "United Nations Office of High Commission for Refugees/UNHCR" ጋር በመተባበር ከኮንሶ፣ አሌ፣ ጋርዱላ እና ጋሞ ዞኖች ከተወጣጡ የፍርድ ቤት ዳኞች ጋር የካቲት 1/2017 ዓ.ም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የገጠር መሬት አዋጅ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ምክክር አካሂዷል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: የሕግ ት/ቤት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የገጠር መሬት አዋጅ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ የምክክር መድረክ አካሄደ

- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ 8ኛውን ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች የውኃ ዋና ምዘና ውድድር በዩኒቨርሲቲው ዋናው ግቢ በሚገኘው ኦሎምፒክ ስታንዳርድ መዋኛ ገንዳ ከጥር 29 - የካቲት 1/2017 ዓ/ም ድረስ አስተናግዷል።ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ 8ኛውን ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች የውኃ ዋና ምዘና ውድድር አስተናገደ

- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከደቡብ ኢትዮጵያ እና ከማእከላዊ ኢትዮጵያ ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮዎች ጋር በመተባበር የአደንዛዥ ዕፅ ተጠቃሚነት መንስዔዎች፣ የሚያስከትለው ጉዳትና የመፍትሔ አቅጣጫዎች ላይ የሠራውን የጥናት ሰነድ ጥር 29/2017 ዓ/ም ርክክብ አካሂዷል፡፡ በዕለቱ ከምርምሩ በተገኙ የመፍትሔ ምክረ ሃሳቦች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: ዩኒቨርሲቲው የአደንዛዥ ዕፅ ተጠቃሚነት መንስዔዎች፣ የሚያስከትለው ጉዳትና የመፍትሔ አቅጣጫዎች ላይ የሠራውን ጥናት አስረከበ

- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እና ሰላም ሚኒስቴር በጋራ በመተባበር ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ሰላምና ጸጥታ ቢሮ እና ከዞኖች ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ለተወጣጡ እንዲሁም ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች፣ መምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞች ጥር 27/2017 ዓ/ም በበጎ ፈቃድ ማኅበረሰባዊ አገልግሎት ጽንሰ ሃሳብ ትግበራና በሀገር ግንባታ መሠረታውያን ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: በበጎ ፈቃድ ማኅበረሰባዊ አገልግሎት ጽንሰ ሃሳብ ትግበራና በሀገር ግንባታ መሠረታውያን ዙሪያ ሥልጠና ተሰጠ
- የዩኒቨርሲቲው ስፖርት ልኡካን ቡድን ደማቅ አቀባበል ተደረገለት
- AMU and AAU Launch Joint Project to Document and Preserve Koegu Language and Culture
- አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኮይጉ ቋንቋና ባህልን ለመሰነድ የትብብር ምርምር ፕሮጀክት ይፋ አደረጉ
- AMU, Sahay Solar Association, HSLU Completed the Advanced Solar Training and Certified the Trainees