- Details
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተከናወኑ የምርምር ሥራዎች ላይ ተመሥርቶ በጫሞ ሐይቅ ተፋሰስ ሥር በሚገኙ 10 ወረዳዎች ዘላቂ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ ለማከናወን በጀርመን ልማት ባንክ፣ በኢትዮጵያ መንግሥት፣ በGIZ እና በማኅበረሰብ ተሳትፎ በሚሸፈን ከ1.8 ቢሊየን ብር በላይ በጀት የሚከናወንና ለ5 ዓመታት የሚቆይ ፕሮጀክት /Sustainable Land Management Project/ ይፋ ሆኗል፡፡ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: ከ1.8 ቢሊየን ብር በላይ የተመደበለት ዘላቂ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ
- Details
አቶ ዮናስ አስፋው ከአባታቸው ከአቶ አስፋው ማዳ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ አስካለች ቦርቾ በቀድሞው ጋሞ ጎፋ ዞን አርባ ምንጭ ከተማ ወዜ ቀበሌ በ1981 ዓ/ም ተወለዱ፡፡
- Details
የዩኒቨርሲቲ-ኢንደስትሪ ትስስርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ከክርስቲያን ኤይድ/Christian Aid/ ጋር በመተባበር ከተለያዩ ጥቃቶች ለመከላከልና የተሞከሩ ወይም የተፈጸሙ ጥቃቶችን ለማስተካከል የሚወሰዱ እርምጃዎችን የሚያሳይ ፖሊሲ ዙሪያ ለዩኒቨርሲቲው ዳይሬክተሮችና ሳይንቲፊክ ዳይሬክተሮች ከነሐሴ 19-20/2014 ዓ/ም ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: በሴፍጋርዲንግ ፖሊሲ/Safeguarding Policy/ ላይ ያተኮረ ሥልጠና ተሰጠ
- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ‹‹International Youth Fellowship›› ከተባለ ግብረ ሠናይ ድርጅት ጋር በአእምሮ ቀረጻ(Mind Set) ዙሪያ በጋራ ለመሥራት የዩኒቨርሲቲው አመራሮችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ሐምሌ 30/2014 ዓ/ም የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡
ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከዓለም አቀፍ ወጣቶች ፌሎውሺፕ/ International Youth Fellowship/ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ
- Details
የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተመራቂ ተማሪዎች በካምባ፣ ገረሴ፣ ቆላ ሼሌ፣ ብርብር፣ ዋጂፎ፣ ቦዲቲና አረካ ጤና ጣቢያዎች በቡድን ሥልጠና ፕሮግራም የቆዩበትን የመስክ ሪፖርት የኮሌጁ ገምጋሚ መምህራን በተገኙበት ነሐሴ 16/2014 ዓ/ም አቅርበዋል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተመራቂ ተማሪዎች የቡድን ሥልጠና ፕሮግራም /Team Training Program/ ሪፖርት አቀረቡ

