ከኢትዮጵያ ጤና አጠባበቅ ማኅበር እና ከ CDC/Center for Disease Control and Prevention/ ጋር በመተባበር የሚሠራው የአርባ ምንጭ ሥነ-ህዝብና ጤና ልማት ማዕከል በ2008 ዓ.ም የሀገር ዓቀፉ INDEPTH አባል ሆኗል፡፡

ምርምር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ካስቀመጧቸው የትኩረት መስኮች አንዱና መሰረታዊ እንደመሆኑ መጠን ተቋሙንና ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ እንዲሁም በገበያ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመገኘት የሚያስችል ነው፡፡

ዩኒቨርሲቲው የሚሰጣቸውን አገልግሎቶችና የአገልግሎት አሰጣጥ መስፈርቱን እንዲሁም አገልግሎቱ የሚሰጥበትን ቦታና ደንበኞች አገልግሎት ለማግኘት በቅድሚያ ማሟላት የሚገባቸውን ቅድመ ሁኔታ በዝርዝር ለተገልጋዮች ለማሳወቅ የዜጎች ቻርተር አዘጋጅቷል፡፡

በዩኒቨርሲቲው ህክምናና ጤና ሣይንስ ኮሌጅ የተቋቋመው “የተዘነጉ የቆላማ አካባቢ በሽታዎች የትብብር ምርምርና ሥልጠና  ማዕከልˮ /Collaborative Research and Training Center for Neglected Tropical Diseases/ የሆድ ጥገኛ ትላትሎች እና ሺሽቶሶሚያሲስ/ቢልሃርዚያ/ በሽታ ህክምና ውጤታማነትን የሚፈትሽ ጥናት አካሂዷል፡፡

የተማሪዎች አገልግሎት ማዕከል ከአ/ምንጭ ተሀድሶ ማዕከል ጋር በመተባበር “አካል ጉዳተኛን ማካተት ወሳኝ ነው፤ ተደራሽነትና ማብቃት ለሁሉምˮ በሚል መሪ ቃል ዓለም ዓቀፉን የአካል ጉዳተኞች ቀን በ21/04/08 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው አክብሯል፡፡