
- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ ብዝኃ ሕይወት ኢንስቲትዩትና "PELUM Ethiopia" ትብብር በተዘጋጀው 2ኛው አገራዊ የዘር እና የምግብ ዐውደ ርእይ ላይ የእንሰት ቴክኖሎጂ የዕውቀት ሽግግር በማድረግ እና የእንሰት ተጠቃሚ ማኀበረሰቦች የምግብ ሥርዓት እንዲሻሻል ላበረከተው የላቀ አስተዋጽዖ ታኅሣሥ 14/2017 ዓ.ም የዕውቅና የምስክር ወረቀትና የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶለታል።ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሕግ ት/ቤት ተማሪዎች ማኅበር ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሙቲንግ ማኅበር እና ከሕግ ት/ቤት ምስለ ችሎት ማስተባበሪያ ቢሮ ጋር በመተባበር ‹‹የኢትዮጵያ የመሬት ባለቤትነት መብት፣ የመንግሥትና የሕዝብ ወይስ የግል? የተሻለው አማራጭ የቱ ነው?›› በሚል ርእስ ከኅዳር 11-12/2017 ዓ/ም ክርክር አካሂደዋል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

- Details
በዩኒቨርሲቲው ስፖርት አካዳሚ አዘጋጅነት ከታኅሣሥ 12/2017 ዓ/ም ጀምሮ በየካምፓሱ በሚገኙ ወንድ ተማሪዎች መካከል የእግር ኳስ ውድድር እየተካሄደ ይገኛል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መካከል የእግር ኳስ ውድድር እየተካሄደ ነው

- Details
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ግብርና ሳይንስ ኮሌጅ በ “Animal Science” ትምህርት ክፍል የ“Animal Production” ትምህርት ፕሮግራም የ3ኛ ዲግሪ ተማሪ ዕጩ ዶ/ር ምትኩ ዮሐንስ ታኅሣሥ 18/2017 ዓ/ም ከጠዋቱ ከ2፡30 ጀምሮ የ3ኛ ዲግሪ ማጠናቀቂያ ምርምር ሥራውን የውጪና የውስጥ ገምጋሚዎችና አማካሪዎች በተገኙበት በዋናዉ ግቢ አዳራሽ ያቀርባል፡፡

- Details
የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የትምህርት ጥራት ዳይሬክተር ለውኃ ቴክኖሎጂ እና ለቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የፕሮግራም ዕውቅና ሥራ ኮሚቴ አባላትና የክፍል ተጠሪ ተማሪዎች ስለ ፕሮግራም ዕውቅና ሥራ ያላቸውን ልምድ ታኅሣሥ 9/2017 ዓ/ም አካፍለዋል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: ለውኃ ቴክኖሎጂ እና ለቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የፕሮግራም ዕውቅና ሥራ ኮሚቴ አባላትና የክፍል ተጠሪ ተማሪዎች ገለጻ ተሰጠ