- Details
የፌዴራል የስነ -ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በአምስቱም ግቢዎች ለሚገኙ ተመራቂ ተማሪዎች ከመጋቢት 21 -25 /2007ዓ/ም ድረስ በሙስና ፅንሰ-ሃሳብ ፣ በስነ-ምግባርና በሙስና ወንጀል ህጎች ላይ ያተኮረ ሥልጠና ሰጥቷል፡፡
የሥልጠናው ዓላማ ተማሪዎቹ ተመርቀው ወደስራ ዓለም በሚቀላቀሉበት ወቅት የተለያዩ ብልሹ አሠራሮች ሊያጋጥሟቸው ስለሚችሉ ከወዲሁ ግንዛቤ ኖሯቸው ራሳቸውን በስነ-ምግባር በማነፅና ሙስናን በመከላከል የተጣለባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ ለማስቻል እንደሆነ የኮሚሽኑ ከፍተኛ አማካሪ አቶ ሙሉነህ ጉግሳ ገልፀዋል ፡፡
ከኮሚሽኑ የመጡት አቶ ሃረጎት አብረሃም የሙስና ወንጀል ምንነትን አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያ፡-ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የማይገባ ጥቅም ለማግኘት ወይም ለማስገኘት ፣ በሌላ ሰው መብት ላይ ጉዳት እንዲደርስ በማሰብ ለመንግስት ሰራተኛ የማይገባ ጥቅም ለመስጠት ቃል የገባ፣ የሰጠ፣ ያቀረበ ወይም ለማቅረብ የተስማማ እንዲሁም በአግባቡ ለተፈፀመ ወይም በአግባቡ ወደፊት ለሚፈፀም የመንግስት ስራ የማይገባ ጥቅምን የሰጠና መሰል ተግባራትን ያከናወነ የሙስና ወንጀል እንደፈፀመ የሚቆጠር መሆኑን አብራርተዋል ፡፡
በተጨማሪም በስልጣን ያለ አግባብ መገልገል፣ የመንግስት ስራን በማያመች መንገድ መምራት ፣በአደራ የተሰጠን ዕቃ ለሌላ ማዘዝ፣በህገ ወጥ መንገድ ገንዘብ መሰብሰብ ፣ ያለአግባብ ጉዳይን ማጓተት፣ ዋጋ ያለውን ነገር ያለ በቂ ክፍያ ማግኘት፣ ያለአግባብ ፈቃድ መስጠትና ማፅደቅ እንዲሁም ምንጩ ያልታወቀ ንብረትና ገንዘብ መያዝ የመሳሰሉት በመንግሥት ሠራተኞች የሚፈፀሙ የሙስና ወንጀሎች መሆናቸውን ጠቁመው ተመራቂ ተማሪዎች በቀጣይ ወደ ስራ አለም ሲገቡ ለሙስና ወንጀል እንዳይጋለጡ ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል ፡፡
ሠልጣኞቹ በሰጡት አስተያየት ጊዜን በአግባቡ አለመጠቀም ፣ስራ ገበታ ላይ በሰዓት ያለመገኘትና ተገቢውን አገልግሎት አለመስጠት፣ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ የሆነ አካሄድ ያለመኖሩ በራሱ ሙስና መሆኑን ተናግረው ስልጠናው በዚህ ሰዓት መሰጠቱ የሙስና ወንጀሎችን ለይተን እንድናውቅና ቅድመ ጥንቃቄ እንድናደርግ የሚያስችለን ነው ብለዋል ፡፡
- Details
You just can’t ignore Mikias Solomon Assefa because of his ordinary look; glint in his eyes and flailing ambition would make you go deeper into his persona. He isn’t tall neither cute, but his achievement is extraordinary!
Read more: Self-belief, positive energy make the way, says Mikias
- Details
‘‘This graduation is special for the first batch of 35 Graduates of Medical Science from College of Medicine and Health Sciences because today AMU is also laying the foundation stone for 300-bedded Referral-cum-Teaching hospital in Arba Minch, said University President, Dr Feleke Woldeyes. Click here to see the Pictures.
Read more: Graduation: Work for nation’s sustainable growth, says Dr Feleke
- Details
Ethiopian contemporary artist Sinafikish Zeleke’s 20 acrylic paintings on display at PG Building Library Hall, Main Campus are optimistic canvas showcasing Ethiopian ethos, cultural spender, social mores and ongoing transition from under-development to self-sufficiency. Click here to view the Pictures.
Read more: Painting Expo: Sinafikish talks peace, unity; instills hope
- Details
የአለም የሚቲዎሮሎጂ ድርጅት / wmo/ ከተቋቋመበት እ.ኤ.አ ከ19 50 ዎቹ ጀምሮ አለም አቀፍ የሚቲዮሮሎጂ ቀን በየዓመቱ መጋቢት 14 / March 23 /የሚከበር ሲሆን በዚህ ዓመት “Climate knowledge for climate action” በሚል መሪ ቃል በአ/ም/ዩ በተፈጥሮ ሣይንስ ኮሌጅ በፓናል ውይይትና በችግኝ ተከላ ተከብሯል ፡፡
የሚቲዎሮሎጂ ቀን ተማሪዎችና መምህራን የወቅቱን የአየር ንብረት ለውጥ እንዲሁም የባህር ነውጦችን መንስኤ በማጥናት በተለይ አርሶ አደሩ በቂ ድጋፍና ግንዛቤ የሚያገኝበትን መንገድ ለማመቻቸት ግኝታቸውን የሚያስተላልፉበት አጋጣሚ መሆን እንዳለበት የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር አጌና አንጁሎ ተናግረዋል ፡፡
የበዓሉ ዋነኛ ዓላማ በሰው ልጆች የእለት ከእለት እንቅስቃሴ የሚፈጠረውን የአየር ንብረት ለውጥ ለመከላከልና ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችን ለመቀነስ የሚያስችሉ ግንዛቤዎችን ለማሳደግ ከሳይንሱ ጋር የተያያዙ መረጃዎችንና እውነታዎችን ማስጨበጥ እንደሆነም የሚቲዎሮሎጂና ሃይድሮሎጂ ትምህርት ክፍል ኃላፊ መ/ር ሙሉጌታ ገናኑ ገልፀዋል ፡በተጨማሪም መምህሩ በሚቲዎሮሎጂ ትምህርት ክፍል እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በዝርዝር አቅርበዋል ፡፡
የሚትዎሮሎጂ ትምህርት ከሁሉም የሳይንስ ትምህርቶች ጋር በቀጥታ ግንኙነት ያለው ዓለም አቀፋዊ ሳይንስ እንደመሆኑ መጠን በጤና ፣በአካባቢ ጥበቃ ፣በንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ የትምህርት ክፍል ነው፡፡ የኮሌጁ ዲን ዶ/ር አለማየሁ ኃ/ሚካኤል ፕሮግራሙን አስመልክተው በሰጡት አስተያየት በዕለቱ የተነሱት ጉዳዮች የሰዎችን ግንዛቤ ከማስፋት አንፃር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያላቸውና አስተማሪ መሆናቸውን በመግለፅ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ከሚደረጉ ጥናትና ምርምር ስራዎች ጎን ለጎን ኮሌጁ በእለቱ የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብ ኃላፊነት እንዳለበትም ተናግረዋል፡፡
ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
አ/ም/ዩ