
- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጀርመን ሀገር ከሚገኘው ዓለም አቀፍ ሮትራክት ድርጅት/Rotary Club Bonn International/ እና ሮተሪ ኢትዮጵያ/Rotary Ethiopia/ ጋር በመተባበር ‹‹Environmental Sustainability, Water and Agroforestry with Permaculture for Gircha in Ethiopia›› የተሰኘና ለሦስት ዓመታት የሚቆይ አዲስ የትብብር ፕሮጀክት በቆጎታ ወረዳ ነሐሴ 20/2015 ዓ/ም ይፋ አድርጓል፡፡ በግብርናና ደን፣ አፈርና ውሃ ጥበቃ፣ ንጽሕናው የተጠበቀ የቤት አሠራርና አያያዝ እና የሶላር ፕላንቶች ጥገና ላይ ሥልጠናዎችን መስጠት፣ በማኅበረሰቡ ቤቶች አስተማሪ ፖስተሮችን ማቅረብ እንዲሁም ለፕሮጀክቱ ውጤቶች ዘላቂነት ትብብሮችን መመሥረት በፕሮጀክቱ ከሚተገበሩ ሥራዎች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በቆጎታ ወረዳ የ5.4 ሚሊየን ብር አዲስ የትብብር ፕሮጀክት ይፋ አደረገ

- Details
ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ AMU-IUC ፕሮግራም ፕሮጀክቶች አንዱ በሆነውና በጤናው ዘርፍ የእናቶችንና ሕፃናትን ጤና ለማሻሻል የሚተገበረው ፕሮጀክት የ3ኛ ዲግሪ ተማሪዎች የምርምር ውጤት የደረሰበትን ደረጃ የማስተዋወቂያ ወርክሾፕ ነሐሴ 18/2015 ዓ/ም ተካዷል፡፡ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: የ‹‹AMU-IUC›› ፕሮጀክት III የ3ኛ ዲግሪ ተማሪዎች የምርምር ውጤት የደረሰበት ደረጃ ማስተዋወቂያ ወርክሾፕ ተካሄደ

- Details
ዕጩ ዶ/ር አበራ ሽጉጤ በአርባ ምንጭ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በ“Water Resource and Irrigation Engineering” ፋካልቲ በ‹‹Irrigation and Drainage Engineering›› ትምህርት ፕሮግራም የ3ኛ ዲግሪ ትምህርቱን ሲከታተል ቆይቷል፡፡ ዕጩ ዶ/ር አበራ የ3ኛ ዲግሪ መመረቂያ ጽሑፉን የውጪና የውስጥ ገምጋሚዎች እንዲሁም አማካሪዎች በተገኙበት በዋናው ግቢ አዲሱ አዳራሽ ነሐሴ 26/2015 ዓ/ም ከጧቱ 2፡30 ጀምሮ የሚያቀርብ ይሆናል፡፡
Read more: የዕጩ ዶ/ር አበራ ሽጉጤ የ3ኛ ዲግሪ (PhD) መመረቂያ ጽሑፍ ግምገማ መርሃ ግብር

- Details
የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ በአርባ ምንጭ ከተማ ሲያካሂደው የነበረው ስብሳባ መጠናቀቅ ተከትሎ የስብሳበው ተሳታፊዎች አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እያከናወነ የሚገኘውን የእንሰት፣ የጫሞ ሐይቅን መልሶ የማልማት እና ሌሎች የምርምር ግኝት ውጤቶች የመስክ ምልከታ ነሐሴ 20/2015 ዓ.ም አካሂደዋል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

- Details
በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ የ2015 ትምህርት ዘመን ሥራ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ መርሃ ግብር ከነሐሴ 19-20/2015 ዓ/ም የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ልማት ዘርፍ ከፍተኛ አመራሮች፣ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዝደንቶችና አካዳሚክ ምክትል ፕሬዝደንቶች በተገኙበት በአርባ ምንጭ ከተማ ኃይሌ ሪዞርት ተካሂዷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
- የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች በጫሞ ሐይቅ ዳርቻ እየተከናወነ የሚገኘውን የሙከራ መልሶ ማልማት ሥራን ጎበኙ
- Eastern and Southern Africa NTD/Trachoma Cross Boarder Partnership held its Annual Meet in Arba Minch
- US Embassy Held Informative Session;Higher Education in USA and Other Related Issues
- ለአሌ ልዩ ወረዳ ማኅበራዊ ፍርድ ቤት ዳኞች በሰብዓዊ መብቶችና ፆታን መሠረት ባደረጉ ጥቃቶች ዙሪያ ሥልጠና ተሰጠ