- Details
የአንደኛውን የእድገትና ትራስፎርሜሽን ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የሁለተኛውን የእድገትና ትራስፎርሜሽን ረቂቅ ዕቅድ እንዲሁም ሌሎች ሀገራዊና ተቋማዊ አጀንዳዎችን ያካተተ ስልጠና ከመስከረም 7/2008 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ሰባት ቀናት ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ሠራተኞች እየተሰሠጠ ይገኛል፡፡ የስልጠናዉ ተሳትፎ በፎቶ የኢትዮጵያ ብሮድ ካስቲንግ ኮሮፖሬሽን ዘገባ
Read more: ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ መምህራን እና ሠራተኞች በሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ ያተኮረ ልዩ ሥልጠና በመሰጠት ላይ ነው
- Details
Ministry of Education in association with Arba Minch University would be holding comprehensive orientation workshop for the academic staff, administrative personnel, senior and fresh students from September 18, 2015.
Read more: Govt. training for academic, admin and students from Sept. 18
- Details
በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት የማድረጊያ ቀን ከመስከረም 24-25 ሲሆን ለነባር የዩኒቨርሲቲው ቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች የምዝገባ ቀን መስከረም 19-20 መሆኑን እያሳወቅን በተጠቀሰው ቀን በኣካል ቀርባችሁ ሪፖርት እንድታደርጉ እንታደርጉ እንገልፃለን፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ለነባር የድህረ-ምረቃ እና የቅድመ- ምረቃ የተከታታይና የርቀት ተማሪዎች ተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 26-27/2008ዓ.ም መሆኑን እየገለፅን አዲስ ለሚመደቡ ወይም ለምንቀበላቸው የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎቸው ወደ ዩኒቨርሲቲው የመግቢያ ቀን በሌላ ማሰታወቂያ የምናሳውቅ ይሆናል፡፡
Click here to download the full information.
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት
- Details
Applied Entrepreneurship Education Program (AEEP), a three-year joint venture of Arba Minch University and Neu-Ulm University of Applied Sciences’ (HNU) completed its second term on Sept. 8, 2015.
Read more: AEEP: AMU-NHU’s venture completes term; prototypes developed
- Details
የዩኒቨርሲቲው የካፒታልና የመደበኛ በጀት አፈፃፀም እየተሻሻለ መምጣቱን የፋይናንስና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አማረ ጋማ ገልጸዋል፡፡
ከ2007 በፊት በነበረው አፈፃፀም በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር በጀት ተመላሽ ይደረግ የነበረ ሲሆን ከ2005 – 2007 የበጀት ዓመታት የነበረው አፈፃፀም በንፅፅር ሲታይ በ2007 የበጀት ዓመት የመደበኛ በጀት አፈፃፀም 98 በመቶ ሲሆን የካፒታል በጀት ደግሞ 92 በመቶ ነበር፡፡በመሆኑም በበጀት ዓመቱ ከመደበኛ እና ካፒታል በጀት በድምሩ 10 በመቶ ወይም 37 ሚሊየን ብር ብቻ ፈሰስ ተደርጓል፡፡
በ2008 የበጀት ዓመት ለዩኒቨርሲቲው የተመደበው የካፒታልና መደበኛ በጀት 1.2 ቢሊየን ሲሆን ካለፉት ዓመታት ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ መሆኑን የገለፁት አቶ አማረ ሁሉም የሥራ ክፍሎች በፋይናንስ ደንብና መመሪያ መሠረት በጀታቸውን 100% መጠቀም ይገባቸዋል ብለዋል፡፡ በተለይም የግዥ ፍላጎቶች በበጀት መዝጊያ ወቅት ተደራርበው በመቅረባቸው ምክንያት ሳይፈፀሙ እንዳይቀሩ የየሥራ ክፍል ኃላፊዎች ክትትል በማድረግ ዕቅዶቻቸውን በወቅቱ አንዲያስፈፅሙ አሳስበዋል፡፡
ዳይሬክቶሬቱ 46 የበጀትና ፋይናንስ ባለሙያዎችን በማቀፍ በመደበኛና ከመደበኛ የሥራ ሠዓት ውጭ ዘወትር ምሽት እስከ ሁለት ሠዓት እንዲሁም በሳምንት መጨረሻ ቀናት ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡