
- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሳውላ ካምፓስ በመደበኛና በሳምንት መጨረሻ ያስተማራቸውን 338 የመጀመሪያና የ2ኛ ዲግሪ ተማሪዎች ሰኔ 26/2016 ዓ/ም ለ7ኛ ጊዜ አስመርቋል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

- Details
በቅርቡ ተመርቆ ሥራ በሚጀምረው በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያ እና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከሰኔ 23-24/2016 ዓ/ም የጽዳት ዘመቻና የምድረ ግቢ ማስዋብ ሥራ ተካሂዷል።
በሥራው ላይ የዩኒቨርሲቲው አመራሮችና ሠራተኞችን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል። ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያ እና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የጽዳት ዘመቻ ተካሄደ

- Details
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ትምህርት መስኮች የ3ኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ የስምንት 3ኛ ዲግሪ ተማሪዎች መመረቂያ ጽሑፎች ከሰኔ 19-21/2016 ዓ/ም የውጭና የውስጥ ገምጋሚዎች እንዲሁም አማካሪዎች በተገኙበት ተገምግሟል፡፡ የ8ቱም ዕጩ ዶክተሮች መመረቂያ ጽሑፎች አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላታቸው በአማካሪ ቦርዱ ተቀባይነት አግኝተው ጸድቀዋል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

- Details
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ትምህርት ቢሮ በ2016 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና አሰጣጥ፣ አስተዳደርና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ጉዳዩ ከሚመልከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ሰኔ 21/2016 ዓ/ም የውይይት መድረክ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ አካሂዷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: በ2016 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና አሰጣጥና አስተዳደር ዙሪያ ክልላዊ የምክክር መድረክ ተካሄደ

- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሠለጠናቸውን ከ2,500 በላይ የቅድመና ድኅረ ምረቃ ተማሪዎች ሰኔ 26/2016 ዓ.ም በጎፋ ሳውላ ከተማ ሳውላ ካምፓስ እና ሰኔ 27/2016 ዓ.ም በአርባ ምንጭ ከተማ አባያ ካምፓስ ያስመርቃል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ባለፉት 36 ዙር ምረቃዎች ከ82,000 በላይ ብቃት ያላቸው ምሩቃንን በማፍራት ለሀገራችን ልማትና እድገት የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ያለ አንጋፋ ተቋም ነው፡፡
Read more: ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሠለጠናቸውን ከ2,500 በላይ ተማሪዎች ለ37ኛ ዙር ሊያስመርቅ ነው