
- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲን ለ2ኛ ዙር በፕሬዝደንትነት ለማገልገል በመሾሜ ከፍ ያለ ደስታ የተሰማኝ መሆኑን በታላቅ አከብሮት እየገለጽኩኝ ዩኒቨርሲቲው ለአካባቢውና ለሀገራችን ዕድገት ከከፍተኛ ትምህርት ተቋም ተልዕኮዎች አኳያ የሚጠበቅበትን በላቀ ደረጃ እንዲያበረክት እንዲሁም የዩኒቨርሲቲውን ደረጃና ዝና ከፍ ለማድረግ ሁላችንም ተቀናጅተንና ተባብረን እንሥራ፡፡
Read more: ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አመራር አካላት፣ መምህራን፣ ተመራማሪዎች፣ የአስተዳደር ሠራተኞች፣ ተማሪዎች እና የቀድሞ ተማሪዎች በሙሉ ከአምዩ...

- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲን ላለፉት ዓመታት በፕሬዝደንትነት ሲመሩ የቆዩት ዶ/ር ዳምጠው ዳርዛ የመጀመሪያ ዙር የሹመት ዘመን መጠናቀቅን ተከትሎ 13 ተፎካካሪዎች የተሳተፉበት ይፋዊ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ተካሂዶ በድጋሚ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ሆነው ተሹመዋል፡፡

- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት ጾታዊ ጥቃትንና ትንኮሳን መከላከል በሚቻልበት መንገድ ላይ ከዋናው ግቢና ከተፈጥሮ ሳይንስ ኮሌጅ የሴት ተማሪዎች ኅብረት አደረጃጀቶች ጋር ከኅዳር 30-ታኅሣሥ 01/2015 ዓ/ም በየካምፓሶቻቸው ውይይት አካሂዷል፡፡ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከ‹‹GIZ››፣ እፉዬ ገላ ኢቨንት ቴክኖሎጂና ኮንሰልተንሲ እና ኢትዮጆብስ ጋር በመተባበር ከኅዳር 22-26/2015 ዓ/ም በጫሞ ሐይቅ ዙሪያ ሀካቶን አካሂዷል፡፡ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ስፖርት አካዳሚ ከደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት የእግር ኳስ ፌዴሬሽን እና ከጋሞ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ጋር በመተባበር ከደቡብ ክልል ለተወጣጡ በሥራ ላይ ያሉ አሠልጣኞች ከኅዳር 20 - 29/2015 ዓ.ም ሲሰጥ የነበረው የ‹‹CAF D License›› የእግር ኳስ አሠልጣኝነት ሥልጠና ተጠናቋል፡፡ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: በአፍሪካ ስፖርት ኮንፌዴሬሽን አዘጋጅነት በዩኒቨርሲቲው ሲሰጥ የነበረው የእግር ኳስ አሠልጣኞች ሥልጠና ተጠናቀቀ