‹‹IT and T-Solutions PLC›› ከሁሉም ካምፓሶች ለተወጣጡ የሬጅስትራር ባለሙያዎች በተማሪዎች ውጤት አያያዝና በSMIS ሶፍትዌር አጠቃቀም ዙሪያ ከግንቦት 6-13 /2011 ዓ.ም ሥልጠና ሰጥቷል፡፡የሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር በለጠ ይልማ እንደገለፁት ሥልጠናው አዳዲስ አሠራሮችን ወደ ሥራ ለማስገባትና ባለሙያዎቹ ብቁ ሆነው እንዲወጡ ለማድረግ የተዘጋጀ ሲሆን በቀጣይ ለዲፓርትመንት ኃላፊዎችና ሌሎች መምህራንም የሚሰጥ ነው፡፡ ምስሉን ለመመልከት ከዚህ ይጫኑ

ሶፍትዌሩ የተማሪዎችን ሙሉ መረጃ ለመያዝ፣ ተማሪዎች የመታወቂያ ቁጥራቸውን በመጠቀም መረጃቸውን በቀላሉ እንዲያገኙ እና የሀሰት መረጃዎችን ለማጣራት የሚያስችል ነው፡፡

ከ2005 ዓ/ም ጀምሮ የተመረቁ ተማሪዎች ሙሉ መረጃ በሶፍትዌሩ አማካኝነት በኤሌክትሮኒክ የመረጃ ቋት እንዲመዘገብ የተደረገ ሲሆን ከ2005 ዓ/ም በፊት ያሉትን ተመራቂ ተማሪዎች መረጃ ሙሉ በሙሉ ወደ ኤሌክትሮኒክ የመረጃ ሥርዓት ለማስገባት እየተሠራ መሆኑን ዶ/ር በለጠ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም የተከታታይና ርቀት እንዲሁም የድኅረ-ምረቃ ተማሪዎች በኢንተርኔት ምዝገባ ሳይጉላሉ ካሉበት መመዝገብ እንዲችሉ የተደረገ ሲሆን በቀጣይ ዓመት ተቋማዊ /OFFICAL/ የትምህርት ማስረጃዎችን የሚፈልጉ በአገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጭ ያሉ ተመራቂ ተማሪዎች አስፈላጊውን ክፍያ በመፈፀም በቀላሉ መረጃቸውን በኢንተርኔት ማግኘት የሚችሉበት አሠራር እንደሚዘረጋም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

የ IT and T-Solutions PLC ሥራ አስኪያጅ አቶ ወንድማገኝ ደስታ ዩኒቨርሲቲው የድርጅቱን ሶፍትዌር በተሻለ መንገድ እንዲጠቀምና አልፎ አልፎ የሚከሰቱ ስህተቶችን ዜሮ ለማድረግ እንሠራለን ብለዋል፡፡
ሠልጣኞች በሰጡት አስተያየት ሥልጠናው በዋናነት ሶፍትዌሩን ሲጠቀሙ የሚገጥሙ ችግሮችን በምን መልኩ መፍታት እንደሚችሉ ያሳየ ነው ብለዋል፡፡

ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት