- Details
የሀገር መከላከያ ሠራዊትን፣ በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ወገኖችንና የዘማች ቤተሰቦችን ለመደገፍ የ2ኛ ደረጃ መምህራንንና ተማሪዎችን በማሳተፍ የተጀመረው ሀገራዊ የድጋፍ ዘመቻ የማጠቃለያ መርሃ-ግብር በዩኒቨርሲቲው ኮሚዩኒቲ ት/ቤት ታኅሣሥ 01/2014 ዓ.ም ተካሂዷል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒቲ ት/ቤት የሀገር መከላከያ ሠራዊት ድጋፍ የማጠቃለያ መርሃ-ግብር አካሄደ
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ማዕከል የዩኒቨርሲቲያችንን ማኅበረሰብ የሀገራችን ብሔራዊ ጉዳዮችን በሚያገኙት ሚዲያ ሁሉ (በዋነኛነት በሶሻል ሚዲያ ላይ) እንዲያስተጋቡና እንዲያስተዋውቁ ማስተባበር ዋና ተግባሩ ነው፡፡ ለዚህም ተግባር ይረዳ ዘንድ የሀገራችንን ብሔራዊ አጀንዳዎች ለዜጎች በስፋት ማስተዋወቅና ግንዛቤ ማስጨበጥ በጣም አስፈላጊና ቀዳሚ ሥራ ነው፡፡
- Details
ዓለም አቀፍ የነጭ ሪባን ቀን ‹‹በሴቶችና ሕፃናት ላይ የሚፈጸሙ የኃይል ጥቃቶችን በመከላከልና በማስቆም አጋርነታችንን እናሳይ!›› በሚል መሪ ቃል ሳውላ ካምፓስን ጨምሮ በዩኒቨርሲቲው ሁሉም ካምፓሶች ከኅዳር 16/2014 ዓ/ም ጀምሮ ተከብሯል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
- Details
ከዛሬ ኅዳር 27/2014 ዓ/ም ጀምሮ ሪፖርት በማድረግ ትምህርት እንድትጀምሩ አጥብቀን እናሳስባለን፡፡
የሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት
- Details
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለሚያስተምሩ ነባር የሕክምና መምህራን ‹‹Case Based Discussion›› በተሰኘ የሕክምና ትምህርት ማስተማሪያና የምዘና ዘዴ ላይ ከኅዳር 27 - ታኅሳስ 1/2014 ዓ/ም ለ5 ተከታታይ ቀናት ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡ የኬዝ አፃፃፍ ዘዴዎች እና ኬዞችን ተጠቅሞ ተማሪዎችን ማስተማርና መመዘን የሥልጠናው የትኩረት ነጥቦች ናቸው፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: ‹‹Case Based Discussion›› በተሰኘ የማስተማሪያና የምዘና ዘዴ ላይ ለሕክምና መምህራን ሥልጠና ተሰጠ

