- Details
በኮምፒዉተር ሳይንስ ትምህርት ክፍል ከ1-4ኛ አመት ድረስ በሚማሩ ተማሪዎች የተሰሩ 16 አዳዲስ የኮምፒዉተር ፕሮግራሞች በዋናዉ ግቢ እና በአባያ ግቢ ከግንቦት 11-12/2007 ዓ.ም ድረስ ለዕይታ ቀርበዋል፡፡
በዓውደ ርዕዩ ለዕይታ ከቀረቡ የኮምፒዉተር ፕሮግራሞች መካከል የዉጪ ሀገርና የሀገር ዉስጥ ጎቢኚዎች ባሉበት ሆነዉ በኢንተርኔት አማካኝነት ሆቴል ለመያዝ፣የአዉቶብስ ቲኬት ለመቁረጥ ፣ ስለቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎች መረጃ ለማግኘት የሚያስችላቸዉና በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በተማሪዎች መመረቂያ ጽሁፎች ዝግጅት ወቅት የሚከሰቱ ኩረጃዎችን ለመቆጣጠር የሚያግዙ ፕሮግራሞች ተጠቃሾች ናቸዉ፡፡
የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዝደንት ዶ/ር ፈለቀ ወልደየስ ኤግዚብሽኑን በጎበኙበት ወቅት እንደተናገሩት በኤግዚብሽኑ የቀረቡት የኮምፒዉተር ፕሮግራሞች ችግር ፈቺ ከመሆናቸዉ በተጨማሪ በተማሪዎች የግል ጥረት መሰራታቸዉ የሚበረታታ ነዉ፡፡ ዶ/ር ፈለቀ አክለዉ ተማሪዎች እንዲህ አይነት ሥራ መስራታቸዉ ከበስተጀርባቸዉ ጠንካራ መምህራን መኖራቸዉንና የዩኒቨርሲቲዉን የትምህርት አሰጣጥ ጥራት የሚያሳይ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ነጋሽ ዋጌሾ በበኩላቸዉ በኤግዚብሽኑ የቀረቡት የፈጠራ ሥራዎች ዓለም በኮምፒዉተር ዕዉቀት የደረሰበት ደረጃ ለመድረስ ከምናከናዉናቸዉ ተግባራት አንዱ አካል መሆኑን ጠቅሰዉ የፈጠራ ሥራዎቹ ወደ ተግባር ሊለወጡ የሚችሉ ናቸዉ ብለዋል፡፡
በአዉደ ርዕዩ ወቅት በተሳታፊዎች በተሰጠዉ ድምጽ አሸናፊ የሆነዉ በተማሪዎች መመረቂያ ጽሁፎች ዝግጅት ወቅት የሚከሰቱ ኩረጃዎችን ለመቆጣጠር የሚያስችል ፕሮግራም በመስራት ለዕይታ ያቀረበዉ-የ4ኛ አመት ተመራቂ ተማሪ አቤል ተመስገን ነዉ፡፡ተማሪ አቤል እነደተናገረዉ ተመራቂ ተማሪዎች መመረቂያ ጽሁፎቻቸዉን በሚያቀርቡበት ወቅት በፊት የተመረቁ ተማሪዎች ከሰሯቸዉ ሥራዎች በተወሰነ መልኩ ኮርጀዉ ስለሚያቀርቡ በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተማሪዎች የተሰሩ ፕሮጀክቶች አንዳንዶቹ ተመሳሳይነት ይታይባቸዋል፡፡ ስለዚህ እሱ የሰራዉ የኮምፒዉተር ፕሮግራም በኢኒስቲትዩቱ የተሰሩ ፕሮጀክቶችን በጠቅላላ መዝግቦ መያዝ ስለሚያስችል ተመሳሳይ ፕሮጀክቶች ሲመጡ በቀላሉ ለይቶ ያሳዉቃል፡፡ኩረጃ በአንድ የኒቨርሲቲ ብቻ የማይወሰን አለም አቀፋዊ እና ሀገር አቀፋዊ ባህሪ ስላለዉ አሁን የሰራዉን ፕሮጀክት በዚህ ደረጃ የማሳደግ ህልም እንዳለዉም ተማሪ አቤል አስምሮበታል፡፡
በአዉደ ርዕዩ መዝጊያ ስነ-ስርአት ላይ የተገኙት የዩኒቨርሲቲዉ መምህራን፣ተማሪዎች እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች በሰጡት አስተያየት እንዲህ አይነት አዉደ ርዕይ መካሄዱ ሌሎችንም ተማሪዎች የሚያነሳሳ መሆኑን በመጥቀስ የአዉደርዕዩ አቅራቢ ተማሪዎች በንድፈ ሀሳብ የተማሩትን ትምህርት በተግባር አሳይተዋል ብለዋል፡፡
- Details
የግንቦት 20 ሃያ አራተኛ አመት የድል በዓል በዋናው ግቢ ግንቦት 26/2007 ዓ.ም ‟ከብተና ስጋት ወደ ለዉጥ አብነት የተሸጋገረች ሀገር - ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል በድምቀት ተከበረ፡፡
የኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፍስሃ በቀለ የግንቦት 20 ፍሬዎችን በተመለከተ ዘርዘር ያለና ሁሉንም ዘርፎች የዳሰሰ የመወያያ ሰነድ ለታዳሚዎች አቅርበዉ ጠለቅ ያለ ዉይይት ተደርጎበታል፡፡በሰነዱ ከግንቦት 20 ድል በኋላ በሀገራችን በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ ፣በመሰረተ ልማት ፣ በዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ እና በሰላምና የውጭ ግንኙነት ዘርፎች የተመዘገቡ ድሎች ተዳስሰዋል፡፡
ሰነዱን መሰረት በማድረግ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ከግንቦት 20 ድል ወዲህ በሀገሪቱ የብሄር፣ የቋንቋ ፣ የባህል፣ የጾታ እና የሃይማኖት ነፃነቶች የተከበሩ ሲሆን በኢኮኖሚ ዕድገት ረገድም አለም ባንክና ሌሎች አለም-አቀፋዊ ተቋማት የመሰከሩለት እድገት የተመዘገበ መሆኑን ጠቅሰዉ እኛም የአይን እማኞች ነን ብለዋል፡፡በተለይም በትምህርትና በጤና ተቋማት ግንባታና ተደራሽነት እንዲሁም በመንገድ ግንባታ፣በቴሌኮሙኒኬሽንና በመብራት ኃይል አቅርቦት የተመዘገቡ ለዉጦች ለሌሎች ሀገራትም ምሳሌ የሚሆኑ ናቸው ብለዋል፡፡ በተጨማሪም አስተያየት ሰጪዎች የተጀመረዉን የህዳሴ ጉዞ ማስቀጠል የሁሉም ኢትዮጵያዊ ኃላፊነት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
በበአሉ አከባበር ስነ-ስርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዝደንት ዶ/ር ፈለቀ ወልደየስ እንደገለፁት ግንቦት 20 ለመላዉ ኢትዮጵያዊያን አንድ የጨለማ ምዕራፍ ተዘግቶ ሌላ አዲስ ብርሃን ፈንጣቂ ምዕራፍ የተጀመረበት ነዉ፡፡በመሆኑም የሀገራችን ህዝቦች በሽምቅ ውጊያ፣በግድያ፣በአፈናና ዉምብድና ከመሰቃየት ወጥተዉ ወደ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ መንገድ ተሸጋግረዋል፡፡
የጋሞ ጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጥላሁን ከበደ በበኩላቸዉ የትግሉ ሰማዕታት የህዝብን አጀንዳ አንግበው ወደ ትግሉ ሲገቡ ለራሳቸው እንደማያልፍላቸውና የህይወት መስዋዕትነት ሊከፍሉ እንደሚችሉ ቢያውቁም ለመጪው ትውልድ ብርሃንን ይፈነጥቁ ዘንድ ተሰውተዋል ብለዋል፡፡ በመሆኑም የዛሬዉ ትዉልድ የህዳሴ ጎዳና ላይ ያለች ሰላማዊ ሀገር በመረከቡ ዕድለኛ ስለሆነ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ሁሉ በአግባቡ በመወጣት ሀገራችን እየተገበረች ለምትገኘዉ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ጉዞ የጀርባ አጥንት መሆን አለበት ሲሉም ተደምጠዋል፡፡በመጨረሻም የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሀገራችን ከግብርና መር ኢኮኖሚ ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ የምታደርገዉን ሽግግር በመማር-ማስተማር፣በምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ከወትሮዉ በበለጠ እንዲደግፍ አሳስበዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲዉ ከፍተኛ አመራሮች፣የአስተዳደርና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች፣መምህራንና ተማሪዎች በበአሉ ላይ የተገኙ ሲሆን የጋሞ ጎፋ ዞን ባህላዊ ኪነት ባንድ የተለያዩ ጣዕመ ዜማዎችን በማሰማት በአሉን አድምቋል፡፡
- Details
This year’s overall topper of Arba Minch University, Tarekegn Tumebo Kariba, is a humble son of a farmer; he is from Kambata Tembaro zone. He has encountered difficulties but didn’t give in on the contrary come out successful.
Read more: Guidance, hard works and determination is the key: AMU topper
- Details
List of top scoring students :-
Read more: INSTITUTE AND COLLEGE-WISE LIST OF TOP-SCORING STUDENTS
- Details
Arba Minch University’s 28th Convocation conducted in the tastefully decorated Auditorium at Abaya Campus on 27th June 2015, has many firsts. Of this year’s 4400 graduates, 4287 were under and 113 post-graduates from 36 different streams. Of total pass-outs, 65% alone were from engineering streams while remaining 35% constituted other subjects.Click here to see the Pictures.
Read more: 28th Convocation: Contribute in nation building, graduates told