
- Details
የዩኒቨርሲቲው የምርምር ዳይሬክቶሬት ከግብርና፣ ከሕክምናና ጤና እንዲሁም ከተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጆች ጋር በመተባበር 7ኛውን ‹‹ሳይንስ ለዘላቂ ልማት›› ሀገር አቀፍ የምርምር ዓውደ ጥናት ከሚያዝያ 8-9/2013 ዓ/ም አካሂዷል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

- Details
የዩኒቨርሲቲው ማኅበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ የማኅበረሰብ አገልግሎት ከጋሞ ዞን ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ጋር በመተባበር ከጋሞ ዞን እና በዞኑ ከሚገኙ 14 ወረዳዎችና 4 ከተማ አስተዳደሮች ለተወጣጡ 37 የቋንቋ ጥናት ባለሙያዎች እንዲሁም ለወረዳና ከተማ አስተዳደር ኃላፊዎች ከሚያዝያ 4 - 7/2013 ዓ/ም በቋንቋ ጥናት ዘዴዎች፣ በመረጃ አሰባሰብ ሂደት፣ በስነ-ቃል እና በስነ-ጽሑፍ ጥናት ላይ ያተኮረ የክሂሎት ማሻሻያ ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

- Details
የዩኒቨርሲቲው ሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት በዓለም ለ110ኛ በኢትዮጵያ ለ45ኛ ጊዜ የተከበረውን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ‹‹የሴቶችን መብት የሚያከብር ማኅበረሰብ እንገንባ›› በሚል መሪ ቃል መጋቢት 30/2013 ዓ/ም በሳውላ ካምፓስ አክብሯል፡፡

- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ብራይት ፊውቸር አግሪካልቸር ፕሮጀክት /BFA/ ‹‹የሥራ ፈጠራ ክሂሎትን ማሳደግ›› በሚል ርዕስ ከተለያዩ ክልሎች የግብርና እና ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኮሌጆች ለተወጣጡ መምህራን ከመጋቢት 23/2013 ዓ/ም ጀምሮ ለተከታታይ 8 ቀናት የአሠልጣኞች ሥልጠና ሰጥቷል፡፡
የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ዶ/ር ይስሃቅ ከቸሮ እንደተናገሩት ሠልጣኞች በራሳቸው ዘርፍ ሥራ እንዲፈጥሩና ለተማሪዎቻቸውም ማሳየት እንዲችሉ ክሂሎታቸውን ለማሳደግ የተዘጋጀ ሥልጠና ነው፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

- Details
የውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በውሃ አቅርቦትና ሳኒተሪ ምኅንድስና የ3ኛ ዲግሪ የትምህርት ፕሮግራም ለማስጀመር ሚያዝያ 2/2013 ዓ/ም የሥርዓተ ትምህርት የውስጥ ግምገማ አካሂዷል፡፡
የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር ዓለማየሁ ጩፋሞ እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው የምርምር ዩኒቨርሲቲ ተብሎ እንደመለየቱ በ2ኛና 3ኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች በትኩረት እየሠራ ይገኛል፡፡ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በሚቀጥሉት 5 ዓመታት 5,000 የ3ኛ ዲግሪ ተማሪዎችን ለማስመረቅ ያቀደ በመሆኑ ዩኒቨርሲቲው ፕሮግራሙን መክፈቱ ለዚህ ሀገራዊ ዕቅድ መሳካት የበኩሉን አስተዋፅኦ የሚያበረክትበት ዕድል የሚፈጥር ነው፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: የዩኒቨርሲቲው ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የሥርዓተ ትምህርት የውስጥ ግምገማ አካሄደ