
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ማኅበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ከኮሌጁ ዩኒቨርሲቲ-ኢንደስትሪ ትስስርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ማስተባበሪያ ጽ/ቤት፣ ከጂኦግራፊና አካባቢ ጥናት ት/ክፍል እንዲሁም ከጀርመን ተራድኦ ድርጅት (GIZ) ጋር በመተባበር ከጋሞ ዞን ወረዳዎች ለተወጣጡ የተፈጥሮ ሀብትና ደን ልማት ባለሙያዎች በ‹‹Geographic Information System(GIS) እና ‹‹Global Positioning System››(GPS) ሶፍትዌሮች ዙሪያ ከሐምሌ 26 - ነሐሴ 1/2013 ዓ/ም ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: ከጋሞ ዞን ወረዳዎች ለተወጣጡ የተፈጥሮ ሀብትና ደን ልማት ባለሙያዎች በ‹‹GIS›› እና ‹‹GPS›› ሶፍትዌሮች ዙሪያ ሥልጠና ተሰጠ

- Details
በዩኒቨርሲቲው የሕግ ትምህርት ቤት ለሚማሩ 59 የ5ኛ ዓመት የሕግ ተመራቂ ተማሪዎች እንዲሁም ከዚህ ቀደም በተለያዩ ቦታዎች የሕግ ትምህርታቸውን ተከታትለው የመውጫ ፈተናውን ላላለፉ 87 ተማሪዎች ከሐምሌ 27-30/2013 ዓ/ም የ2013 ዓ/ም ሀገር አቀፍ የሕግ መውጫ ፈተና ተሰጥቷል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሀገር አቀፍ የሕግ መውጫ ፈተና /Exit Exam/ ተሰጠ
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የድኅረ-ምረቃ ትምህርት ቤት በ2014 የትምህርት ዘመን በመደበኛ፣ በማታ እና በሳምንት መጨረሻ መርሃ-ግብር መስፈርቱን የሚያሟሉ አዲስ አመልካቾችን ከዚህ በታች በተጠቀሱት የትምህርት መስኮች ተቀብሎ ማሠልጠን ይፈልጋል፡፡

- Details
በጫሞ ሐይቅ ዙሪያ ለሚሠራው አሳታፊ ዘላቂ የመሬትና የውሃ አያያዝ ሥራ ዕቅድ አዘገጃጀት ላይ ያተኮረ ሥልጠና ከ10 ወረዳዎች ለተወጣጡ 58 የልማት ጣቢያ ሠራተኞችና የዘርፉ ባለሙያዎች ከሐምሌ 13/2012 ዓ/ም ጀምሮ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዓባያ ካምፓስ ለ7 ቀናት ተሰጥቷል፡፡ ሥልጠናው በጀርመን ልማት ተራድኦ ድርጅት/GIZ/ እና በግብርና ሚኒስቴር የዘላቂ መሬት አያያዝ ፕሮጀክት ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር ያዘጋጁት ነው፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: በአሳታፊ ዘላቂ የመሬትና የውሃ አያያዝ ሥራ ዕቅድ አዘገጃጀት ላይ ያተኮረ ሥልጠና ተሰጠ
- Details
በ1ኛ ዓመት የክረምት መርሃ-ግብር ለመመዝገብ አመልክታችሁ የስም ዝርዝራችሁ በማስታወቂያ ሠሌዳ የተገለፀ ተማሪዎች የትምህርት ክፍያና የምዝገባ ጊዜ ከነገ 29/11/2013 - 1/12/2013 ዓ.ም በመሆኑ በተከታታይና ርቀት ትምህርት ኮሌጅ ሬጅስትራር ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በመቅረብ የማስታወቂያ ሠሌዳው ላይ የተለጠፈውን የትምህርት ክፍያ ዝርዝር በማየት ክፍያ እየፈፀማችሁ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን፡፡
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተከታታይና ርቀት ት/ኮሌጅ