
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ልኡካን ቡድን በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት በመካሄድ ላይ ባለው የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ስፖርት ፌስቲቫል ላይ ጥር 24/2017 ዓ/ም በተካሄደው የሴቶች የቼዝ ፍጻሜ ውድድር በሳምራዊት ግርማ አማካኝነት የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳልያ እና ዋንጫ አግኝቷል።ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከፌዴራል ጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የወባ በሽታ በስፋት ከሚታይባቸው ትግራይ፣ አማራ፣ ኦሮሚያ፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች ለተወጣጡ የወባ ፕሮግራምን ለሚያስተባብሩ የጤና ባለሙያዎች /Malaria focal person/ ከጥር 19/2017 ዓ/ም ጀምሮ ለአንድ ወር የሚቆይ የወባ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ላይ ያተኮረ ሥልጠና /Comprehensive Malariology Training/ በመስጠት ላይ ነው፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: ከተለያዩ ክልሎች ለተወጣጡ የጤና ባለሙያዎች የተቀናጀ የወባ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ላይ ያተኮረ ሥልጠና እየተሰጠ ነው

- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ለዩኒቨርሲቲው ክበባት ተጠሪ ተማሪዎች ጥር 20/2017 ዓ/ም በኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከል ዙሪያ የሕይወት ክሂሎት የአሠልጣኞች ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: ለዩኒቨርሲቲው ክበባት ተጠሪ ተማሪዎች በኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከል ዙሪያ የሕይወት ክሂሎት የአሠልጣኞች ሥልጠና ተሰጠ

- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ስፖርት ውድድር በጥር 23/2017 ዓ/ም ውሎ በወንዶች እግር ኳስ ጨዋታ ሰላሌ ዩኒቨርሲቲን 6 ለ 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍጻሜ መቀላቀል ችሏል። በተጨማሪም በወንዶች አትሌትክስ በ200ሜ በተማሪ ማቤል ቱት አማካኝነት የነሐስ ሜዳሊያ እንዲሁም በ400ሜ የዱላ ቅብብል በተማሪ ማቤል ቱት፣ ዳንኤል ተፈራ፣ ያሬድ ታደሰ እና ቴዎድሮስ ጌትነት አማካኝነት ተጨማሪ የነሐስ ሜዳሊያ ማግኘት ተችሏል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ስፖርት ውድድር በወንዶች እግር ኳስ ስፖርት ግማሽ ፍፃሜን ተቀላቀለ

- Details
AMU hosted an enlightening lecture featuring Architect Rahel Shawl, a pioneering architect and founder of RAAS Architects P.L.C, at AMU on January 27, 2025. Attendees were invited to explore Rahael's innovative design philosophy aptly named “Architecture with Care" through an in-depth examination of her landmark, Halala Kella Project. Click here to see more photos.