- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ድህረ ምረቃ ት/ቤት ለ2013 ዓ/ም የትምህርት ዘመን በመደበኛ እና በሳምንት መጨረሻ መርሃ ግብር መስፈርቱን የሚያሟሉ አዲስ አመልካቾችን እየመዘገባ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ የምዝገባ ጊዜ የተራዘመ መሆኑን ባሳወቅነው ማስታወቂያ የመግቢያ ፈተና ጊዜ ወደ ፊት እንደሚገለፅ የተነገረ ሲሆን በዚሁ መሠረት ለሁሉም አመልካቾች የመግቢያ ፈተና የሚሰጠው በድህረ ምረቃ ት/ቤት ሕንፃ መስከረም 25/2013 ዓ/ም ከሰዓት ከ08፡00 ጀምሮ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- Details
UIL & TT Executive Director has planned to undertake the transfer of new technologies and/or adopts the already existing ones to industries/community in 2013 E.C fiscal year.
In line with this, if you have any problem solving idea or technology to be conveyed to our society/industry, submit your proposal until 15 October 2020 to:
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ለዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝደንት ከዩኒቨርሲቲው መምህራን መካከል አወዳድሮ ለመመደብ ይፈልጋል፡፡
የአመልካቾች ትምህርት ደረጃ ሁለተኛ ዲግሪ እና ከዚያ በላይ ሆኖ ከማመልከቻቸው ጋር ቀጥሎ የተዘረዘሩ ማስረጃዎችን በማያያዝ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
Read more: በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝደንትነት ውድድር የወጣ የውስጥ ማስታወቂያ
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የብዝሃ-ሕይወት ምርምርና ጥበቃ ማዕከልና የእንሰትና የመድኃኒት ዕፅዋት ምርምርና ጥበቃ ፓርክ የአካባቢውን ሥነ-ምህዳር በጠበቀ መልኩ የምርምር ሥራዎችን እየከናወነ ነው፡፡
የብዝሃ-ሕይወት ምርምርና ጥበቃ ማዕከል ዳይሬክተርና የሆርቲካልቸር ት/ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰር ሰይፉ ፈቴና የምርምር ማዕከሉ በዋናነት የዘር ምንጭ ሆኖ ለምርምርና ለማስተማሪያነት እያገለገለ የሚገኝ ሲሆን የአካባቢውን ሥነ-ምህዳር በጠበቀ መልኩ የእንሰት ዝሪያዎችን በመንከባከብና በመጠበቅ እንዲሁም በእንሰት ዝሪያዎች ላይ የሚከሰቱ አንዳንድ ችግሮችን በሳይንሳዊ መንገድ ጥናትና ምርምር በማካሄድ በመለየት ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት እየተሠራ ነው፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: የብዝሃ-ሕይወት፣ የእንሰትና የመድኃኒት ዕፅዋት ምርምርና ጥበቃ ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸው ተገለፀ
- Details
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በ<<Public Health Nutrition>> እና በ<<Clinical Bio-Chemistry>> የ2ኛ ዲግሪ የትምህርት ፕሮግራም ለመክፈት የሚያስችል የውጭ ሥርዓተ-ትምህርት ግምገማ መስከረም 7/2013 ዓ/ም አካሂዷል፡፡
የአካዳሚክ ጉ/ም/ፕሬዝደንት ተወካይ ዶ/ር ንጉሴ ታደገ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው በቅርቡ እንደ ሀገር ከተለዩ 8 የምርምር ዩኒቨርሲቲዎች መካከል መሆኑን አስታውሰው መሰል የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች መከፈታቸው ዩኒቨርሲቲው የተሰጠውን ተልዕኮ እንዲወጣ ከማድረግ አንፃር ፋይዳቸው የጎላ ነው ብለዋል፡፡ በዩኒቨርሲቲው የሚከፈቱ አዳዲስና ነባር የትምህርት ፕሮግራሞችን ጥራት ለማረጋገጥም በትኩረት ይሠራል ብለዋል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ2013 የት/ዘመን በህክምናና ጤናው ዘርፍ ሁለት የማስተርስ ዲግሪ ፕሮግራሞችን ሊከፍት ነው