
- Details
Arba Minch University (AMU) got awarded €389,790/Over 45.4 million/ grant from the EU SIFA Innovation Funding Window III for its project entitled "Job Opportunity for Female Employability through the Adoption of Proven Enset Technologies" (JOB-FEET). The project was developed by a team of multidisciplinary professionals from AMU and other institutions. Click here to see more photos.
- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ“SIFA/Skills Initiative for Africa-Funding Window III” በሙከራ የተረጋገጡ የእንሰት ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ለሴቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር በቀረጸው ፕሮጀክት አሸናፊ በመሆን ከአፍሪካ ኅብረት የልማት ኤጀንሲ(African Union Development Agency/AUDA-NEPAD) ጋር ነሐሴ 15/2016 ዓ/ም በአዲስ አበባ አፍሪካ ኅብረት አዳራሽ የጋራ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡ ስምምነቱን ተቋሞቻቸውን ወክለው የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ትብብር ም/ፕሬዝደንት ተባባሪ ፕ/ር በኃይሉ መርደኪዮስ እና የኔፓድ “NEPAD” ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ናርዶስ በቀለ ተፈራርመዋል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያ እና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በቅርቡ ተመርቆ በተወሰኑ የሕክምና ዘርፎች በይፋ ሥራ መጀመሩ ይታወሳል፡፡ ሆስፒታሉ ቀደም ብሎ እየሰጠ ካለው የሕክምና አገልግሎቶች በተጨማሪ ከዛሬ ነሐሴ 10/2016 ዓ/ም ጀምሮ የጥርስ፣ የኤም.አር.አይ/MRI Machine/ እና የሥነ ደዌ/Pathology/ የሕክምናና ምርመራ አገልግሎችን ያስጀመረ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሙያ ማበልጸጊያ ማዕክል ከደረጃ ዶት ኮም/Dereja.com/ እና ከማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር ከጋሞ ዞን የተለያዩ ወረዳዎችና ከአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር በ2015/16 ዓ.ም በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀው በዞኑ ሥራ ዕድል ፈጠራና ልማት ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ለተመዘገቡ ከ270 በላይ ሥራ ፈላጊ ወጣቶች ከነሐሴ 3/2016 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ወራት የሚቆይ የ"Deraja Academy Accelerator Program (DAAP)" ሰዋዊና ሙያዊ ክሂሎት ሥልጠና እየሰጠ ነው፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: ዩኒቨርሲቲው ለሥራ ፈላጊ ወጣቶች በሰዋዊና ሙያዊ ክሂሎት ዙሪያ ሥልጠና እየሰጠ ነው

- Details
በዛሬው ፈጣን ዓለም ባላሰለሰ ትምህርት እና የክሂሎት ዕድገት ውስጥ መሳተፍ ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ እጅግ አስፈላጊነቱ ግልጽ ሲሆን በዕረፍት ላይ ላላችሁ ተማሪዎች፣ ለወጣት ባለሞያዎች፣ ራሳቸሁን በዕውቀት በመገንባት በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር በጎ ተፅዕኖ ለመፍጠር ለምትጓጉ ሁሉ የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ ፕሮጀክት ቀዳሚ ሊያደርጋችሁ ተሰናድቶላችኋል። የትምህርት እና የዕውቀት መነሻችሁ እና ያላችሁበት ደረጃ ምንም ይሁን ያላችሁን ክሂሎት ለማሳደግም ሆነ አዲስ ነገር ለማወቅ ለምትሹ ሁሉ ሰፊ የእድል በር ተከፍቶላችኋል። በመላው ኢትዮጵያ ያላችሁ የክሂሎት አበልፃጊዎች፣ አሳዳጊዎች፣ ዩኒቨርሲቲዎች ይህንን ፕሮጀክት እና እንቅስቃሴዎቹን የሚደግፉ ይሆናል።
ውድ ባለተሰጥዖዎች፣ የኢትዮጵያችን ጥንካሬ በእናንተ እድገት ላይ የተመሠረተ ነው። ለመመዝገብ: http://www.ethiocoders.et