
- Details
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ምርምርና ማኅበረሰብ ጉድኝት ዳይሬክቶሬት አማካኝነት በምርምርና ማኅበረሰብ ጉድኝት ዘርፎች ላይ ትኩረት አድርገው የተዘጋጁ 35 ንድፈ-ሃሳቦች ቀርበው ከጥቅምት 24-25/2015 ዓ/ም ግምገማ ተካሂዶባቸዋል፡፡ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: በምርምርና ማኅበረሰብ ጉድኝት ዘርፎች ላይ ያተኮሩ የምርምርና የማኅበረሰብ ጉድኝት ንድፈ-ሃሳቦች ተገመገሙሙ

- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ጽ/ቤት ከዩኒቨርሲቲው ለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር ለዩኒቨርሲቲው ካውንስል አባላት ግምገማዊ የሥልጠና መድረክ ጥቅምት 22/2015 ዓ/ም አዘጋጅቷል፡፡ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

- Details
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በሂሳብ ት/ክፍል በ“Operation Research” ትምህርት ፕሮግራም የ3ኛ ዲግሪ ተማሪ ዕጩ ዶ/ር ሀብታሙ ፀጋዬ ነገ ቅዳሜ ኅዳር 03/2015 ዓ.ም ከረፋዱ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ በዓባያ ካምፓስ በፒ.ኤች.ዲ. አዳራሽ እንዲሁም በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ በማኔጅመንት ት/ክፍል በ“Marketing Management” ትምህርት ፕሮግራም የ3ኛ ዲግሪ ተማሪ ዕጩ ዶ/ር ስንታየሁ አሰፋ ረቡዕ ኅዳር 7/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በዋናው ግቢ መሰብሰቢያ አዳራሽ የመመረቂያ ፅሑፎቻቸውን በማቅረብ የሚያስገመግሙ ይሆናል፡፡ በመድረኩም የውጭና የውስጥ ገምጋሚዎችና አማካሪዎች ይገኙበታል፡፡

- Details
ትምህርት ሚኒስቴር ከሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ለተወጣጡ የመረጃና መገናኛ ቴክኖሎጂ ዳይሬክተሮችና የሲስተም አስተዳደር ባለሙያዎች ‹‹Federated Identity System and Educational Roaming›› በሚል ርዕስ ከጥቅምት 24-26/2015 ዓ/ም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: ለመረጃና መገናኛ ቴክኖሎጂ ዳይሬክተሮችና የሲስተም አስተዳደር ባለሙያዎች ሥልጠና ተሰጠ

- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ19/12/2ዐ14 ዓ.ም በምክትል ፕሬዝደንትነት ማዕረግ የውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር አወዳድሮ ለመሰየም ባወጣው ማስታወቂያ መሠረት ከተመዘገባችሁት ተወዳዳሪዎች ዝቅተኛውን መስፈርት በማሟላት በመመሪያው መሠረት ከስር በስም የተገለጻችሁ ተወዳዳሪዎች ኅዳር 6/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ለሚከናወነው ፓናል ኢንተርቪው እና ስትራቴጅክ ዕቅድ ገለፃ የተመረጣችሁ በመሆኑ በስም ዝርዝሩ ቅደም ተከተል መሠረት በተከታታይ ስለምታቀርቡ በተጠቀሰው ቀን በአዲሱ የስብሰባ አዳራሽ በሰዓቱ እንድትገኙ እናስታውቃለን፡፡