ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና የአስተዳደር ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች በመሉ፡- በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚካሄደው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማህበረሰብ ስልጠና ለዩኒቨርሲቲያችን መምህራንና የአስተዳደር ድጋፍ  ሰጪ ሠራተኞች ከመስከረም 05-12/2009 ዓ/ም በተለያዩ ካምፓሶች በተዘጋጁ ጊዜያዊ መድረኮች የሚሰጥ በመሆኑ ሁሉም ተሳታፊ በየምድብ የስልጠና መድረክ ያለመንጠባጠብ በጊዜ በመገኘት የስልጠናው ተካፋይ እንዲሆን በአጽንዖት ያሳስባል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

ዩኒቨርሲቲው ከደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ/ አርብቶ አደር ጉዳዮች ቢሮ ጋር በመተባበር በአነስተኛ መስኖ አስተዳደርና አጠቃቀም ለ6 ወራት ያሠለጠናቸውን 30 ሠልጣኞች ግንቦት 13/2008ዓ.ም አስመርቋል፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከዩናይትድና ከብራይት ኮንስትራክሽን ድርጅቶች ጋር የ2ኛ ዙር የሳውላ ካምፓስ የግንባታ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ውል ሰኔ 28/2008 ዓ.ም ተፈራርሟል፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ከህግ ት/ቤት ጋር በመተባበር በደቡብ ኦሞ ዞን ለሚገኙ የማረሚያ ቤት ኃላፊዎችና ሠራተኞች በመሰረታዊ የታራሚዎች መብትና አያያዝ ሰኔ 10/2008 ዓ.ም የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ሰጥቷል፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ህብረት የ2008 ዓ/ም የበጀትና ዕቅድ አፈፃፀምን አስመልክቶ ሰኔ 12/2008 ዓ/ም ግምገማ አካሂዷል፡፡ የተማሪዎች ህብረት ተተኪ ሥራ አስፈፃሚ አባላት ምርጫም ተከናውኗል፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡