የተቀናጀ የትምህርትና ቴክኖሎጂ አመራርን ለማጠናከር ከሁሉም ካምፓስ የተወጣጡ የ1ለ5ና የልማት ቡድን ተጠሪ ተማሪዎች እንዲሁም የአደረጃጀቱ አስተባባሪ መምህራን መጋቢት 04/2008 ዓ/ም ከተቋማዊ ለውጥ ዳይሬክቶሬትና ከፕሬዝደንት ጽ/ቤት ጋር ውይይት አካሂደዋል፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

የኘሬዝደንት ጽ/ቤት እና ም/ኘ/ጽ/ቤቶች እንዲሁም ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የ2008 በጀት ዓመት የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ ሚያዝያ 5/2008 ዓ/ም አካሂደዋል፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፀጥታና ደህንነት ጽ/ቤት ከጋሞ ጎፋ ዞን ፖሊስ መምሪያ ጋር በመቀናጀት ለ150 የፀጥታና ደህንነት አባላት በወንጀል ምንነትና መከላከል፣ በመሳሪያ አያያዝና አጠቃቀም እንዲሁም ሰልፍ ላይ ያተኮረ ስልጠና ከመጋቢት 8/2008 ዓ/ም ጀምሮ ለ7 ተከታታይ ቀናት ሰጥቷል፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

የሰው ሀብት አስተዳደርና ልማት ዳይሬክቶሬት ከፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር ጋር በመቀናጀት ለዳይሬክቶሬቱ ባለሙያዎች በሰው ሀብት አስተዳደር ጉዳዮች አፈፃፀም በ17/07/2008 ዓ/ም የአንድ ቀን ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡