- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሙያ ማበልጸጊያ ማዕክል ከደረጃ ዶት ኮም/Dereja.com/ እና ከማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር ከጋሞ ዞን የተለያዩ ወረዳዎችና ከአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር በ2015/16 ዓ.ም በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀው በዞኑ ሥራ ዕድል ፈጠራና ልማት ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ለተመዘገቡ ከ270 በላይ ሥራ ፈላጊ ወጣቶች ከነሐሴ 3/2016 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ወራት የሚቆይ የ"Deraja Academy Accelerator Program (DAAP)" ሰዋዊና ሙያዊ ክሂሎት ሥልጠና እየሰጠ ነው፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: ዩኒቨርሲቲው ለሥራ ፈላጊ ወጣቶች በሰዋዊና ሙያዊ ክሂሎት ዙሪያ ሥልጠና እየሰጠ ነው
- Details
በዛሬው ፈጣን ዓለም ባላሰለሰ ትምህርት እና የክሂሎት ዕድገት ውስጥ መሳተፍ ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ እጅግ አስፈላጊነቱ ግልጽ ሲሆን በዕረፍት ላይ ላላችሁ ተማሪዎች፣ ለወጣት ባለሞያዎች፣ ራሳቸሁን በዕውቀት በመገንባት በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር በጎ ተፅዕኖ ለመፍጠር ለምትጓጉ ሁሉ የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ ፕሮጀክት ቀዳሚ ሊያደርጋችሁ ተሰናድቶላችኋል። የትምህርት እና የዕውቀት መነሻችሁ እና ያላችሁበት ደረጃ ምንም ይሁን ያላችሁን ክሂሎት ለማሳደግም ሆነ አዲስ ነገር ለማወቅ ለምትሹ ሁሉ ሰፊ የእድል በር ተከፍቶላችኋል። በመላው ኢትዮጵያ ያላችሁ የክሂሎት አበልፃጊዎች፣ አሳዳጊዎች፣ ዩኒቨርሲቲዎች ይህንን ፕሮጀክት እና እንቅስቃሴዎቹን የሚደግፉ ይሆናል።
ውድ ባለተሰጥዖዎች፣ የኢትዮጵያችን ጥንካሬ በእናንተ እድገት ላይ የተመሠረተ ነው። ለመመዝገብ: http://www.ethiocoders.et
- Details
Background
This PhD supervision training is initiated by the Ethiopian SuperStars project. The Ethiopian Superstars is an international training program that involves 7 Ethiopian universities (Addis Ababa University, Ambo University, Arba Minch University, Bahir Dar University, Hawassa University, Jimma University and Mekelle University). The project is coordinated by Jimma University and Ghent University, is financially supported by VLIR-UOS (www.vliruos.be) and runs from September 2023 to August 2026. The overall vison of Ethiopian SuperStars project is strengthening the advisory and coaching skills of academic staff at Ethiopian higher education institutions. To realize this, Ethiopian SuperStars works towards the following four milestones:
Read more: A Call for PhD SUPERVISION Training Applicants - 2024
- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ የመሬት መንሸራተት አደጋ በተከሰተበት ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ የደረሰውን የመሬት መንሸራተት አደጋ አስመልክቶ ከተለያየ ዘርፍ የተወጣጡ ተመራማሪዎችን ወደ ቦታው በመላክ የአደጋውን መንስኤና ቀጣይ የአደጋ ስጋቶች እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ሥነ ልቦናዊ ጉዳቶችን ለማወቅ ያካሄደው ፈጣን የዳሰሳ ጥናት ያለበት ደረጃ ነሐሴ 06/2016 ዓ/ም የዩኒቨርሲቲው አመራሮችና ተመራማሪዎች በተገኙበት ቀርቦ ተገምግሟል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: የመሬት መንሸራተት አደጋ በደረሰበት ገዜ ጎፋ ወረዳ እየተካሄደ የሚገኘው የዳሰሳ ጥናት ያለበት ደረጃ ተገመገመ
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሁሉ አቀፍ ሴክተር ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ከዩኒቨርሲቲው የተለያዩ ካምፓሶች ለተወጣጡ ተማሪዎች ከሐምሌ 30 - ነሐሴ 3/2016 ዓ/ም የአእምሮ ውቅር ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: የሁሉ አቀፍ ሴክተር ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ለዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች የአእምሮ ውቅር ሥልጠና ሰጠ
- ‹‹Vita/RTI-Ethiopia›› ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የዕፅዋት ማበልጸጊያ ምርምር የሚያግዙ የላቦራቶሪ ግብአቶች ድጋፍ አደረገ
- ሀገር አቀፍ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የትምህርት አመራርና መምህራን ልዩ ሥልጠና በተጠናከረ ሁኔታ እየተሰጠ ነው
- ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያ እና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሠራተኞችና ባለሙያዎች ሥልጠና ተሰጠ
- AMU Secures £50,000 Grant from British Museum to Document Enset Food System