- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ካውንስል አባላት፣ የፌዴራል ፖሊስ አባላት፣ የአስተዳደር ሠራተኞችና ተማሪዎች በተገኙበት በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ላንቴ ቀበሌ በአንድ ጀምበር 600 ሚሊየን ችግኞች ለመትከል የተያዘው ሀገራዊ መርሃ ግብር አካል የሆነ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ነሐሴ 17/2016 ዓ/ም ተካሂዷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: ሀገራዊው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ
- Details
በየዓመቱ በኢትዮጰያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት የሚካሄደው የታዳጊ ወጣቶች እግር ኳስ ውድድር ዘንድሮ ለ3ኛ ጊዜ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ከሐምሌ 10/2016 ጀምሮ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: 3ኛው የታዳጊ ወጣቶች የእግር ኳስ ውድድር በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እየተካሄደ ነው
- Details
Arba Minch University (AMU) got awarded €389,790/Over 45.4 million/ grant from the EU SIFA Innovation Funding Window III for its project entitled "Job Opportunity for Female Employability through the Adoption of Proven Enset Technologies" (JOB-FEET). The project was developed by a team of multidisciplinary professionals from AMU and other institutions. Click here to see more photos.
- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ“SIFA/Skills Initiative for Africa-Funding Window III” በሙከራ የተረጋገጡ የእንሰት ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ለሴቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር በቀረጸው ፕሮጀክት አሸናፊ በመሆን ከአፍሪካ ኅብረት የልማት ኤጀንሲ(African Union Development Agency/AUDA-NEPAD) ጋር ነሐሴ 15/2016 ዓ/ም በአዲስ አበባ አፍሪካ ኅብረት አዳራሽ የጋራ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡ ስምምነቱን ተቋሞቻቸውን ወክለው የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ትብብር ም/ፕሬዝደንት ተባባሪ ፕ/ር በኃይሉ መርደኪዮስ እና የኔፓድ “NEPAD” ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ናርዶስ በቀለ ተፈራርመዋል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያ እና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በቅርቡ ተመርቆ በተወሰኑ የሕክምና ዘርፎች በይፋ ሥራ መጀመሩ ይታወሳል፡፡ ሆስፒታሉ ቀደም ብሎ እየሰጠ ካለው የሕክምና አገልግሎቶች በተጨማሪ ከዛሬ ነሐሴ 10/2016 ዓ/ም ጀምሮ የጥርስ፣ የኤም.አር.አይ/MRI Machine/ እና የሥነ ደዌ/Pathology/ የሕክምናና ምርመራ አገልግሎችን ያስጀመረ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡