የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ መምህራን ከጃፓይጎ(Jhpigo) ኢትዮጵያ ጋር በመተባባር ባጎለበቱት የሥርዓተ ትምህርት መቆጣጠሪያና አተገባበር ቴክኖሎጂ  ዙሪያ ሚያዝያ 11/2016 ዓ/ም ውይይት ተካሂዷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

AMU’s partner Alabaster International team has visited the Progress of the Collaborative Research Project entitled ‹‹ Evaluation and promotion of cultivated and wild ENSET for climate change adaptations and utilization through value addition and industrialization of products in Ethiopia and Kenya ›› being executed in partnership with Alabaster International, AMU, EBI, JKUAT, and the Girl Child Network from April 15-19, 2024. Click here to see more photos.

አርባ ምንጭ የዩኒቨርሲቲ ሕግ ትምህርት ቤት ከተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ከፍተኛ ኮምሽን ጋር በመተባበር በሽግግር ፍትሕ ሂደት ዙሪያ ወጣቶች፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች መምህራን እንዲሁም ተማሪዎች ያላቸውን ሚና አስመልክቶ ሚያዝያ 15/2016 ዓ/ም ገለጻ አካሂዷል፡፡

በ17/08/2016 ከ8:00 ጀምሮ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ለዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች በኢንተርፕርነርሽፕ ዙሪያ ያተኮረ ልዩ መርሃ ግብር ተዘጋጅቷል። በዝግጅቱ ላይ ታዋቂው የቢዝነስ አማካሪ እና ደራሲ ዶ/ር ወሮታው በዛብህ ተገኝተው የኢንተርፕርነርሽፕ የተግባር ተሞክሯቸውን ያካፍላሉ። በተጨማሪ በዕለቱ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መካከል የቢዝነስ ሃሳብ ውድድር ይካሄዳል። የተሻለ ሃሳብ ያቀረቡ ተማሪዎችም ይሸለማሉ:: ስለሆነም ሁሉም የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በዚህ ሁነት ላይ እንድትገኙ የተጋበዛችሁ መሆኑን እናሳውቃለን።