
- Details
ለ1 ወር በተለያዩ ጤና ጣቢያዎች በቡድን ሥልጠና ፕሮግራም/Team Training Program/TTP/ ላይ የቆዩ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተመራቂ ተማሪዎች የመጨረሻ ሪፖርታቸውን ገምገሚ መምህራን በተገኙበት ከመስከረም 14-15/2014 ዓ/ም መስክ በወጡባቸው ጤና ጣቢያዎች አቅርበዋል፡፡ ቆላ ሼሌ፣ ኮንሶ ካራት፣ አረካ፣ ቦዲቲና ብርብር ጤና አጠባበቅ ጣቢያዎች ተማሪዎቹ በሥራ የቆዩባቸው የጤና ተቋማት ናቸው፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተመራቂ ተማሪዎች የቡድን ሥልጠና ፕሮግራም /Team Training Program/TTP/ ሪፖርታቸውን አቀረቡ

- Details
በአርባ ምንጭ ከተማ ለሚገነባው የአረጋውያንና ሕፃናት ማዕከል ገቢ ማሰባሰቢያ ‹‹ኑ የነገ ቤታችንን እንሥራ›› በሚል መሪ ቃል መስከረም 11/2014 ዓ/ም በአርባ ምንጭ ከተማ የማነቃቂያ የእግር ጉዞ ተካሂዷል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: በአርባ ምንጭ ከተማ ለሚገነባው የአረጋውያንና ሕፃናት ማዕከል ገቢ ማሰባሰቢያ የማነቃቂያ የእግር ጉዞ ተካሄደ

- Details
ረ/ፕ አባይነህ ኡናሾ ከአባታቸው ከአቶ ኡናሾ ጋንዲሌ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ፋስቴ ጡኖ በቀድሞው ጋሞ ጎፋ ጠቅላይ ግዛት ጋርዱላ አውራጃ ዘይሴ አካባቢ በ1950 ዓ/ም ተወለዱ፡፡

- Details
ረ/ፕ ጊሹ ሰሙ ከአባታቸው አቶ ሰሙ ተሊላ እና ከእናታቸው ወ/ሮ የሺ ኡርጌ ሰኔ 12/1968 ዓ/ም በቀድሞው አርሲ ክፍለ ሀገር በአርባ ጉጉ አውራጃ ልዩ ስፍራው ጮሌ በምትባል ቦታ ተወለዱ፡፡