
- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ፣ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲና የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ‹‹Effects of Active Rifting and Thermal uplift on Climate, Soil, Water and Agriculture in Southern Main Ethiopian Rift: Implementing Strategies for Recovery Improvement›› በሚል ርእስ በሦስቱ ተቋማት በተመደበ 12 ሚሊየን ብር የሚሠራ ግራንድ የትብብር ምርምር ፕሮጀክት ጥር 24/2017 ዓ/ም ይፋ አድርገዋል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

- Details
በየዓመቱ የምርምር ሥራዎች ያሉበትን ደረጃ ለመገምገም ጉባኤ የሚያዘጋጀው አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ 12ኛውን ዓመታዊ የምርምር ሥራዎች ግምገማ ወርክሾፕ ጥር 23/2017 ዓ/ም አካሂዷል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ 12ኛውን ዓመታዊ የምርምር ሥራዎች ግምገማ ወርክሾፕ አካሄደ

- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማኅበረሰብ ጉድኝትና ዩኒቨርሲቲ-ኢንደስትሪ ትስስር ዳይሬክቶሬት ከጋሞ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ጋር በመተባበር ከተለያዩ አካባቢዎች ለተወጣጡ ወጣቶች ከጥር 19-23/2017 ዓ/ም የሰብእና ልኅቀት ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ልኡካን ቡድን በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት በመካሄድ ላይ ባለው የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ስፖርት ፌስቲቫል ላይ ጥር 24/2017 ዓ/ም በተካሄደው የሴቶች የቼዝ ፍጻሜ ውድድር በሳምራዊት ግርማ አማካኝነት የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳልያ እና ዋንጫ አግኝቷል።ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከፌዴራል ጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የወባ በሽታ በስፋት ከሚታይባቸው ትግራይ፣ አማራ፣ ኦሮሚያ፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች ለተወጣጡ የወባ ፕሮግራምን ለሚያስተባብሩ የጤና ባለሙያዎች /Malaria focal person/ ከጥር 19/2017 ዓ/ም ጀምሮ ለአንድ ወር የሚቆይ የወባ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ላይ ያተኮረ ሥልጠና /Comprehensive Malariology Training/ በመስጠት ላይ ነው፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: ከተለያዩ ክልሎች ለተወጣጡ የጤና ባለሙያዎች የተቀናጀ የወባ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ላይ ያተኮረ ሥልጠና እየተሰጠ ነው