የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ማኅበረሰብ በቅርቡ በሞት ለተለዩት መ/ር ወርቁ ውበት የተሰማውን ሐዘን ለመግለጽ ሐምሌ 16/2013 ዓ.ም የሻማ ማብራት ፕሮግራም አካሂዷል፡፡ በፕሮግራሙ በአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝደንት፣ በኮሌጁ ዲን፣ በመምህራንና በተማሪዎች በንግግር፣ በጽሑፍና በግጥም የሐዘን መግለጫ ቀርቧል፡፡  ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

ሀገራችን ኢትዮጵያ በመንግሥትና በሕዝብ ሁለንተናዊ ተሳትፎ እየገነባች የሚገኘው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 2ኛው ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት በመጠናቀቁ መላው የዩኒቨርሲቲያችን ማኅበረሰብና ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን ደስ አለን!!

ግድቡ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለሀገራችን ዕድገት መፋጠን በሙሉ አቅም አገልግሎት መስጠት እስኪጀምር ለግንባታው የነበረው ሁለንተናዊ ሕዝባዊ ተሳትፎ ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል። አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲና ማኅበረሰቡም እንደ ከዚህ ቀደም ሁሉ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ቀሪ የግንባታ ሥራዎች እስከሚጠናቀቁ ድረስ አስፈላጊውን ሁሉ አስተዋፅዖ ማድረጋቸውን አጠናክረው የሚቀጥሉ መሆኑን አረጋግጣለሁ።

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ2014 በጀት ዓመት ዓመታዊ ዕቅድ የዩኒቨርሲቲው ካውንስል አባላት በተገኙበት ሐምሌ 15/2013 ዓ/ም ተገምግሞ ጸድቋል፡፡ ከካውንስል አባላቱ በዕቅዱ ላይ ሊሻሻሉ፣ሊካተቱና ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገቡ ነጥቦች ቀርበዋል፡፡  ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ