የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሕግ ትምህርት ቤት የማኅበረሰብ ጉድኝት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከጋሞ ዞን ፍትሕ መምሪያ ጋር በመተባበር በዞኑ ከሚገኙ ሦስት የከተማ አስተዳደሮችና አራት ወረዳዎች ዐቃቤያን ሕጎች፣ ወንጀል መርማሪ ፖሊሶች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በወንጀል በተጠረጠሩ፣ በተያዙ እና በተከሰሱ ሰዎች መብቶች ዙሪያ ግንቦት 12/2015 ዓ/ም ውይይት አካሂዷል፡፡ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ላይ በደረሰው ድንገተኛ የትራፊክ አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ መምህራን የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን በመላው የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ስም ይገልጻል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ለመምህራኑ ቤተሰቦች፣ ዘመዶችና የሥራ ባልደረቦች እንዲሁም ለመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ መጽናናትን ይመኛል፡፡

በጫሞ ሐይቅ ረግረጋማ ስፍራና የሐይቁ የላይኛው ተፋሰስ አካል በሆነው ጌዣ ደን ውስጥ ምርምርን መሠረት ያደረገ የመልሶ ማልማት የሙከራ /Pilot/ ፕሮጀክት አካላዊና ሥነ-ሕይወታዊ ሥራዎች ተስፋ ሰጪ ውጤት እያሳዩ መሆኑ ተመልክቷል፡፡ የሙከራ ፕሮጀክቱ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከሮማንና ኃይለማርያም ፋውንዴሽን፣ ከቤልጂየሙ ኬዩሊዩቨን ዩኒቨርሲቲ/KU Leuven University/ እና ቢኦኤስ+/BOS+/ ከተሰኘ ድርጅት ጋር በመተባበር የተጀመረ ሲሆን ከጀርመን ልማት ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ለሚሠራው ለአምስት ዓመታት የሚቆይ ፕሮጀክት እንደ ማሳያ የሚያገለግል ነው፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ከአርባ ምንጭ ከተማ ሴቶችና ሕጻናት ጉዳዮች ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ከከተማው አስተዳደር ለተወጣጡ የሥራ ኃላፊዎች የአመራርነት ሥልጠና ግንቦት 4/2015 ዓ/ም ሰጥቷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

 

Arba Minch University Senate promoted six academic staff to Associate Professorship Academic Rank position on May 11/2023. Click here to see more pictures!