- Details
በ2016 ዓ/ም በቅድመ-ምረቃ ከዩኒቨርሲቲው ለተመረቁ 5 ግለሰቦች ነፃ የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርት ዕድል ለመስጠት ተወስኗል፡፡ በመሆኑም ከዩኒቨርሲቲው በ2016 ትምህርት ዘመን በከፍተኛ ውጤት የተመረቃችሁ እና ሀገር አቀፍ የሁለተኛ ዲግሪ መግቢያ ፈተና ተፈትናችሁ የማለፊያ ሰርተፊኬት የያዛችሁ ተመራቂዎች በዕድሉ መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ከመስከረም 28 እስከ ጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በሥራ ሰዓት የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት ውጤት መረጃ እና የሀገር አቀፍ ሁለተኛ ዲግሪ ትምህርት መግቢያ ፈተና ውጤት ሰርተፊኬት በመያዝ በዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራርና አሉምናይ ዳይሬክቶሬት ጽ/ቤት ቀርባችሁ እንድትመዘገቡ ዩኒቨርሲቲው ይገልፃል፡፡
- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ‹‹e-SHEን›› አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ ያዘጋጀ በመሆኑ ከሥር በተቀመጠው የጊዜ ሠሌዳ መሠረት በየካምፓሶቻችሁ በመገኘት እንድትከታተሉ እናስታውቃለን፡፡
በዕለቱ ክላስ አይኖርም! ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
- Details
የ3ኛ ዓመት የፋርማሲ ተማሪ የሆነችው ተማሪ ሜሮን ካፒታ ዋልጬ ባጋጠማት የኩላሊት ሕመም በሕክምና እየተረዳች ቢሆንም ጉዳዩ ከአቅም በላይ በመሆኑ ወደ ውጭ ሀገር (ሕንድ) ተልካ የኩላሊት ንቅለ ተከላ እንዲደረግላት በሐኪሞች ተወስኗል፡፡
- Details
Arba Minch University/AMU/ - Institutional University Cooperation /IUC/ project, has recently trained its PhD students and other AMU staff on the usage of a highly versatile drone camera system to enhance research capabilities across various fields from September 15-21, 2024. The advanced drone camera technology, one of the IUC’s second phase outreach program, aims to equip researchers with cutting-edge tools for conducting sophisticated, data-driven researches in agriculture, environmental conservation, and water quality assessment. Click here to see more photos.
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በዕውቀትና ቴክኖሎጂ የተደገፈ የፍትሕ ሥርዓት ለማስፈን የሚረዳ የፎረንሲክ ምርመራ ማዕከልን የሥራ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር መስከረም 13/2017 ዓ/ም አካሂዷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡