- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማኅበረሰብ ጉድኝት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ተክሉ ወጋየሁ የ2014 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና የአፈታተን ሥርዓቱ ያልተለመደና ስርቆትን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር የተቻለበት በመሆኑ እንደሀገር ለመጀመሪያ ጊዜ የመጣው የተማሪዎች ውጤት የትምህርት ሥርዓቱ ምን እንደሚመስል ቁልጭ አድርጎ አሳይቷል ብለዋል፡፡ ከ8 መቶ ሺህ በላይ ተፈታኝ ተማሪዎች 3.3% ብቻ ተማሪ ማለፊያ ነጥብ ማምጣቱ እንደሀገርም ሆነ እንደከፍተኛ ተቋም የሚሠሩ ብዙ ሥራዎች እንደሚጠብቁን ያመላከተ ፈተና መሆኑን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: የትምህርት ጥራትንና የተማሪዎችን ውጤት በዘላቂነት ለማሻሻል የትምህርት ዘርፍ ባለድርሻዎች ቅንጅት እንደሚያስፈልግ ተገለጸ
- Details
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ማኅበራዊ ሳይንስና ስነሰብ ኮሌጅ በእንግሊዝኛ ቋንቋና ስነጽሑፍ ት/ክፍል በ‹‹English Language Teaching (ELT)›› ትምህርት ፕሮግራም የ3ኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩት ዕጩ ዶ/ር ጋሻው ተፈራ እና ዕጩ ዶ/ር ተፈሪ ሀቱዬ የመመረቂያ የምርምር ሥራቸውን የውጪና የውስጥ ገምጋሚዎችና አማካሪዎቻቸው በተገኙበት ጥር 24 እና 25/2015 ዓ/ም አቅርበዋል፡፡ የሁለቱም ዕጩ ዶክተሮች የመመረቂያ ጽሑፎች በአማካሪ ቦርዶቹ ተቀባይነትን አግኝተዋል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: የዕጩ ዶ/ር ጋሻው ተፈራ እና የዕጩ ዶ/ር ተፈሪ ሀቱዬ የ3ኛ ዲግሪ መመረቂያ ጽሑፎች ተገመገሙ
- Details
የጋሞ ዞን አስተዳደር አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ በጋንታ ኦቾሌ ቀበሌ የሚገኘውን ሦስት ሄክታር የጫሞ ሐይቅ ረግረጋማ መሬት መልሶ እንዲለማ ለሌቶ ዓሣ አስጋሪዎች ማኅበር ጥር 22/2015 ዓ.ም በይፋ አስረክቧል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጨኑ፡፡
Read more: የጫሞ ሐይቅ ረግረጋማ ስፍራን መልሶ ለማልማት የሚያስችል ሦስት ሄክታር መሬት ተሰጠ
አርባ ምንጭ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ህንድ ሀገር ከሚገኘው ሂንዱስታን የቴክኖሎጂና ሳይንስ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር የበይነመረብ የምርምር ዓውደ ጥናት አካሄደ
- Details
የአርባ ምንጭ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የስነሕንፃና ከተማ ፕላን ፋከልቲ ሕንድ ሀገር ከሚገኘው ሂንዱስታን የቴክኖሎጂና ሳይንስ ኢንስቲትዩት ጋር በመሆን በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን የምርምር ዓውደ ጥናት ከጥር 22-23/2015 ዓ/ም በበይነመረብ አካሂዷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ1979 ዓ/ም ከተመሠረተ ጀምሮ አያሌ ኢትዮጵያውያንን በውሃ ምኅንድስና ዘርፍ ቀዳሚ አድርጎ ሲያሠለጥን የቆየ ሲሆን ወደ ዩኒቨርሲቲነት ካደገበት ከ1996 ዓ/ም ጀምሮ በበርካታ የምኅንድስና፣ የጤና፣ የግብርና፣ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ፣ የማኅበራዊ ሳይንስና ስነሰብ፣ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ እንዲሁም በሕግ እና በስነትምህርትና ስነባህሪ ዘርፎች ምሁራንን በማፍራት ላይ የሚገኝ ተቋም ነው፡፡ ምስሎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: በ2015 የትምህርት ዘመን ወደ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለምትመጡ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች በሙሉ