በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በማኅበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ በጂኦግራፊና አካባቢ ጥናት ት/ክፍል በ‹‹ Disaster Risk Management›› ትምህርት ፕሮግራም የ3 ዲግሪ ተማሪ ዕጩ ዶ/ር አሸናፊ ኃይሉ ሐሙስ ጥር 04/2015 ዓ/ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ የመመረቂያ ምርምር ሥራውን የውጪና የውስጥ ገምጋሚዎችና አማካሪዎች በተገኙበት በዋናዉ ግቢ መሰብሰቢያ አዳራሽ ያቀርባል፡፡  

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የኢኮኖሚክስ ት/ክፍል በ ‹‹Development Economics›› ትምህርት ፕሮግራም የ3 ዲግሪ ተማሪ ዕጩ ዶ/ር ኤዞ ኤማኮ ማክሰኞ ታኅሣሥ 25/2015 ዓ/ም የምርምር ሥራውን የውጪና የውስጥ ገምጋሚዎችና አማካሪዎች በተገኙበት አቅርቧል፡፡ የመመረቂያ ጽሑፉም አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላት በአማካሪ ቦርዱ ተቀባይነትን አግኝቷል፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

‹‹በሀገር ግንባታ ላይ የምሁራን ሚና›› በሚል መሪ ቃል የዩኒቨርሲቲው ካውንስል እና መምህራንና የአካዳሚክ ቴክኒክ ረዳቶች ከታኅሣሥ 24-27/2015 ዓ/ም የሚቆይ ሀገራዊ ውይይት እያካሄዱ ይገኛል፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ‹‹iCog Anyone Can Code›› ከተሰኘ ድርጅት፣ ከኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር እና ከሁዋዌ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ጋር በመተባበር በአርባ ምንጭ ከተማ ካሉ ልማት፣ ጫሞ፣ ዓባያና አርባ ምንጭ 2 ደረጃና መሠናዶ ት/ቤቶች ለተወጣጡ ተማሪዎች ከታኅሣሥ 20 - ጥር 5/2015 ዓ/ም የሚቆይ ዲጂትረክ/ DigiTruck/ በተሰኘ ፕሮጀክት የአይ ሲ ቲ ሥልጠና እየሰጠ ነው፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲና ክርስቲያን ኤይድ የተሰኘ ግብረ ሠናይ ድርጅት በገቡት ውል መሠረት ዩኒቨርሲቲው የእንሰት አመራረትና ማብላላት ሂደትን የሚያሻሽሉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን አምርቶ ታኅሣሥ 22/2015 ዓ/ም ለድርጅቱ አስረክቧል፡፡ ቴክኖሎጂዎቹ ከድርጅቱ በተገኘ 3.2 ሚሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍ የተመረቱ ሲሆን በወላይታ ዞን እንሰት አብቃይ በሆኑ አካባቢዎች የሚሰራጩ ናቸው፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡