
- Details
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሚገኘው የአምዩ አዩሲ ፕሮጀክት ንዑስ ፕሮጀክት ሁለት ከኮንሶና ጋርዱላ ዞኖች እንዲሁም ከገረሴ ወረዳ ለተወጣጡ የአደጋ እና ስጋት አስተዳደር፣ የተፈጥሮ ጥበቃ፣ የምግብ ዋስትና ባለሙያዎች እና ሞዴል አርሶ አደሮች ‹‹የአደጋ እና ስጋት አስተዳደር በግብርና ዘርፍ›› በሚል ርእስ ከሰኔ 5-6/2017 ዓ/ም በኮንሶ ካራት ከተማ ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ማኅበረሰተብ ጉድኝት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከባዮና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን ቸሀ ወረዳ በዘርፉ ለተሰማሩ ማኅበር አባላት በዘመናዊ የእንሰት መፋቂያ ማሽኖች አጠቃቀም ዙሪያ ከሰኔ 2-6/2017 ዓ.ም ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

- Details
የዩኒቨርሲቲው ሕግ ት/ቤት ‹‹Improving the Observance of the Rights of Accused Persons and Criminal Investigation, Rights of Prisoners and the Treatment of Juvenile Delinquents in the Ethiopian Criminal Justice System: the Case of Gamo and Gofa Zones›› በሚል ርእስ ያከናወነው ግራንድ ጥናት ላይ ሰኔ 07/2017 ዓ/ም የማረጋገጫ ዐውደ ጥናት አካሂዷል፡፡ ጥናቱ በመ/ር ዳግም ወንድሙ ዋና ተመራማሪነት እንዲሁም በመ/ር አብርሃም ክንፈ፣ መ/ርት ንግሥት ግርማ እና Dr. Sam Ponniah ተባባሪ ተመራማሪነት የተከናወነ ነው።ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

- Details
ከመላው ኢትዮጵያ የተወጣጡ የጤናው ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ሰኔ 6/2017 ዓ/ም የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ እና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን የሥራ እንቅስቃሴና ግብዓቶች ጎብኝተዋል።ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: የጤናው ዘርፍ ባለድርሻ አካላት የዩኒቨርሲቲውን ማስተማሪያና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ጎበኙ

- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከ‹‹ኢነርጂ አሲስታንስ/Energy Assistance›› ጋር በመተባበር በጋሞ ዞን ዲታ ወረዳ ጎዛ ቀበሌ በጎዛ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ1.8 ሚሊዮን ብር ወጭ ያሠራው 10 ኪሎ ዋት ኃይል ማመንጨት የሚያስችል የሶላር ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ሰኔ 2/2017 ዓ/ም ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምራል።ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: ዩኒቨርሲቲው በ1.8 ሚሊየን ብር ያሠራው የሶላር ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ
- Advocacy Meeting Held at Dorze Health Center: Health Seeking Behavior of the Community towards Cutaneous leishmaniasis (Bolbo) on Agenda
- Arba Minch University (AMU) School of Law Wins Best Memorial Award at ICRC National Moot Court Competition
- በዶርዜ ጤና ጣቢያ በማኅበረሰቡ የቦልቦ ሕክምና አጠቃቀም ዙሪያ ውይይት ተካሄደ
- AMU College of Agricultural Sciences (CAS) Hosts International Workshop on Scientific Writing and Publication