የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማኅበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ የዩኒቨርሲቲ ኢንደስትሪ ትስስርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከጂኦግራፊና አካባቢ ጥናት ትምህርት ክፍል ጋር በመተባበር ከጋሞ ዞን ዕቅድና ፕላን መምሪያ፣ አየር ንብረትና አስተዳደር ጽ/ቤት፣ ቴክኒክና ሙያ መምሪያ፣ ኢንተርፕራይዝ መምሪያ፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂ መምሪያ፣ ከተማ ልማት፣ ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት፣ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ፣ ጤና መምሪያ እና ጋሞ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ለተወጣጡ ባለሙያዎች በ‹‹GIS››፣ ‹‹GPS›› እና ሪሞት ሴንሲንግ ሶፍትዌሮች ዙሪያ ከሰኔ 7-11/2013 ዓ.ም ሥልጠና ሰጥቷል::  ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የዩኒቨርሲቲው ማኅበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ማኅበረሰበሰ አገልግሎት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከምራብ ዓባያና ከአርባ ምንጭ ከተማ ለተወጣጡ የ1ኛ ደረጃ ት/ቤቶች እንግሊዝኛ ቋንቋ መምህራን ግንቦት 14/2013 ዓ/ም የተማሪዎች የእንግሊዝኛ ቋንቋ ንባብ ክሂሎት ማሻሻያ ዙሪያ ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ በሥልጠናው የእንግሊዝኛ ቋንቋ ፊደላት፣ ድምጽና ስያሜያቸው እንዲሁም ተነባቢና አናባቢ ድምጾች በቃላት ውስጥ ሲገቡ የሚያመጡትን ለውጥ ለተማሪዎቹ የሚያስተምሩበት ስነ-ዘዴ በስፋት ተዳሷል፡፡  ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የዩኒቨርሲቲው ስፖርት አካዳሚ ከፌዴራልና ከደቡብ ክልል ስፖርት ኮሚሽኖች ጋር በመተባበር ከጋሞ ዞን ወረዳዎችና አርባ ምንጭ ከተማ ለተወጣጡ የስፖርት ባለሙያዎችና የስፖርት መምህራን ከሰኔ 2-11/2013 ዓ/ም የጤናና አካል ብቃት እንቅስቃሴ የአሠልጣኞች ሥልጠና ሰጥቷል፡፡  ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሥራ ፈጠራ ልማት ማፍለቂያ ማዕከል ከአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር ሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ዘርፍ ጽ /ቤት ጋር በመተባበር ለአርባ ምንጭ ከተማ ስራ አጥ ወጣቶች በመሠረታዊ ሥራ ፈጠራ ክሂሎት ላይ የሥራ ፈጠራ ማነቃቂያ ሥልጠና ሰኔ 11/2013 ዓ.ም ሰጥቷል፡፡ ሥልጠናው ውስጣዊ ተነሳሽነት እንዲፈጠር የማነቃቂያ ሃሳቦች፣ መሠረታዊ የሥራ ፈጠራ ክሂሎት፣ የቢዝነስ ዕቅድ አዘገጃጀት እና መልካም አጋጣሚዎችን ወደ ሥራ ፈጠራ ሃሳብ መቀየር በሚያስችሉ ነጥቦች ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል፡፡  ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

Program: Biodiversity Conservation and Management
Title: Ecology of Small Mammals Human-Modified Habitats Near the Western Shore of Lake Abaya, Southern Ethiopia
Monday: 28 June 2021 @ 3:00 PM