የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ2015 የትምህርት ዘመን የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም (Remedial) ማጠቃለያ ውጤት በመረጃ መረብ (Online) የተለቀቀ ስለሆነ ከታች የቀረበውን ሊንክ በመጫን (ወይም ሊንኩን በዌብ ፔጅ ላይ ኮፒ-ፔስት በማድረግ)፣ መለያ ቁጥር (ID Number) በማስገባት፣ Search እና View Result በመጫን ማየት የሚትችሉ መሆኑን እየገለጸ በውጤቱ ላይ ቅሬታ ያለው ተማሪ ካለ ከሰኞ እስከ ረቡዕ (ከነሐሴ 1 እስከ 3/ 2015 ዓ.ም) ባለው ጊዜ ውስጥ አካዳሚክ ፕሮግራም ዳይሬክተር ቢሮ (የአምዩ አስተዳደር ሕንጻ 2ኛ ፎቅ) ማመልከት የሚችል/ትችል መሆኑን ያሳውቃል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ2012 ባች የመውጫ ፈተና የወሰዱና ቀሪ ኮርሶችን በቀጣይ መስከረም የሚያጠናቅቁ ተማሪዎች ነሐሴ 5/2015 ዓ.ም ወደ ዩኒቨርሲቲው እንዲገቡ እየገለጸ ከተጠቀሰው ቀን በፊትም ሆነ በኋላ የሚመጡ ተማሪዎችን ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን ከወዲሁ ያሳውቃል፡፡

Arba Minch University held a kick-off meeting on July 22, 2023 to officially launch a 2.3 million ETB collaborative Project with the theme of “Production, Popularization, and Commercialization of Value added Enset-Based Food Products through the Adoption of Proven Processing -Technologies". Click here to see more pictures.

መምህር ሀብታሙ ሻቴ ከአባታቸው አቶ ሻቴ ዮሻ እና ከእናታቸው ወ/ሮ ባዩሽ በቀለ ታኅሣሥ 19/1972 ዓ/ም በቀድሞው ጋሞ ጎፋ አውራጃ ካምባ ወረዳ ተወለዱ፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በካምባ ባዮ 1 ደረጃ ት/ቤት እንዲሁም የ2 ደረጃ ትምህርታቸውን በአርባ ምንጭ አጠቃላይ 2 ደረጃ ት/ቤት ተከታትለዋል፡፡

አርባ ምጭ ዩኒቨርሲቲ ለተመደቡ የሁለተኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ የ12 ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ስለፈተና አሰጣጥና በግቢ ውስጥ ስለሚኖራቸው ቆይታ ዛሬ ሐምሌ 24/2015 ዓ/ም ገለጻ (Orientation) ተሰጥቷል፡፡ ዩኒቨርሲቲው በስድስቱም ካምፓሶቹ 6,546 ወንድ እና 4,857 ሴት በድምሩ 11,403 ተማሪዎች የተቀበለ ሲሆን በትምህርት ሚኒስቴር መርሃ ግብር መሠረት ፈተናውን ከሐምሌ 25/2015 ዓ/ም ጀምሮ የሚወስዱ ይሆናል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡