አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እንግሊዝ ሀገር ከሚገኙት ‹‹Centre for Crop Health and Protection /CHAP›› እና ‹‹SWaDE Technology Company›› ጋር በመተባበር በጋሞ ዞን ጋርዳ ማርታ ወረዳ ቦሄ ቀበሌ ባዞ ወንዝ ላይ ለመስኖ አገልግሎት የሚውል 3.3 ኪሎ ዋት ኃይል የሚያመነጭ በፀሐይ ኃይል የሚሠራ የኃይል ማመንጫ ተከላ አድርጓል፡፡ ተከላው ሦስቱ ተቋማት ‹‹Optimizing Energy Demand in Rural Communities via Precision Agriculture Technology›› በሚል ርእስ እያከናወኑ የሚገኙት የምርምርና ልማት ፕሮጀክት የሙከራ ሥራ ነው፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

ከአሜሪካን ሀገር ኮሎራዶ ስቴት/Colorado State/ ዩኒቨርሲቲ የመጡት የግብርና ኤክስቴንሽን መ/ርና ተመራማሪ ፕ/ር አሰፋ ገብረአምላክ በማኅበረሰብ ጉድኝት፣ በዩኒቨርሲቲ-ኢንደስትሪ ትሰስር እንዲሁም በተዛማጅ ምርምሮች ዙሪያ ተሞክሮን ትኩረት ያደረገ ሥልጠና የካቲት 25/2016 ዓ/ም ለዩኒቨርሲቲው ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ሰጥተዋል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ለ113 በሀገራችን ለ48 ጊዜ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ‹‹ሴቶችን እናብቃ፤ ልማትና ሰላምን እናረጋግጥ›› በሚል መሪ ቃል የካቲት 27/2016 ዓ/ም አክብሯል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በሒሳብ ት/ክፍል በ‹‹Numerical Analysis›› ትምህርት ፕሮግራም የ3ኛ ዲግሪ ትምህርቱን ሲከታተል የቆየው ዕጩ ዶ/ር ወንድምአገኘሁ ስምዖን የካቲት 26/2016 ዓ/ም የምርምር ሥራውን የውጪና የውስጥ ገምጋሚዎች እንዲሁም አማካሪዎች በተገኙበት አቅርቧል፡፡ የመመረቂያ ጽሑፉም አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላት በአማካሪ ቦርዱ ተቀባይነት አግኝቷል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

በሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የኅብረተሰብ ጤና ትምህርት የ2ኛ ዲግሪ ተማሪዎች የልማታዊ ቡድን ሥልጠና ፕሮግራም (DTTP) በአርባ ምንጭ ከተማ ውስጥ በመናኸሪያ ግቢ የተከናወኑ የንጹሕ መጠጥ ውኃ መስመር ዝርጋታና የመንገደኞች ጊዜያዊ ማረፊያ እንዲሁም በሴቻ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ግቢ የተገነባው አነስተኛ ለHIV/AIDS ተጋላጭ ለሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች የቅድመ መከላከያና ማማከሪያ አገልግሎት መስጫ ማዕከል የዩኒቨርሲቲው አመራሮችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የካቲት 23/2016 ዓ/ም ለማኅበረሰቡ የማስተላለፍ መርሃ ግብር ተካሂዷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ